ምዕራፍ 19

1 አክዓብ እቤቱ ሲደርሰስ ኤልያስ ያደረገውን ለሚስቱ ለኤልዘቤል ነገራት፡፡ የበአል ነቢያትን ሁሉ ኤልያስ እንደገደላቸውም ነገራት፡፡ 2 ስለዚህ ኤልዛቤል ይህን መልእክት ለኤልያስ ላከች “እነዚያን የበዓል ነቢያት እንደገደልካቸው ነገ በዚህ ሰዓት ገድልሀለሁ አማልክት በሞት ይቅስፉኝ” 3 ኤልያስ መልእክቱ በደረሰው ጊዜ ፈራ እንዳይገደልም አገልጋዩን አስከትሎ ሸሸ ይሁዳ ውስጥ እስከአለው እስከ ቤርሳቤህ ርቆ ወደ ደቡብ ሸሸ፡፡ አገልጋን እዚያ ተወው፡፡ 4 ከዚያም ብቻውን ወደ ደቡብ ርቆ ወደ በረሀው ሄደ፡፡ቀኑን ሙሉ በእግሩ ከተጓዘ በኋላ ክትክታ ዛፍ ሥር ተቀመጠና እንዲሞት እግዚአብሔር ይፈቅድለት ዘንድ ጸለየ እንዲህ አለ “እግዚአብሔር ሆይ አሁንስ በቃኝ፡፡ እንድሞት ፍቀድልኝ ከቀድሞ አባቶቼ አልበልጥምና፡፡” 5 ከዚያም ክትክታ ዛፍ ሥር ጋደም አለና እንቅልፍ ወሰደው፡፡ ተኝቶ ሳለ አንድ መልአክ ነክቶ አነቃውና “ተነሥ ትንሽ ምግብ ብላ አለው” 6 ኤልያስ ዙሪያውን ሲመለከት በጋሉ ድንጋዮች የተጋገረ ትንሽ ዳቦ አየ፡፡ በገንቦ ውሀም ተመለከተ እና ትንሽ ዳቦ ከበላና ውሃ ከጠጣ በኋላ እንደገና ሊያንቀላፋ ጋደም አለ፡፡ 7 ያኔ ከእግዚአብሔር የተላከው መልዓክ መጥቶ ነካውና “ተነሥና ትንሽ ተጨማሪ ምግብ ብላ ምክንያቱም ረጅም እርቀት ለመጓዝ የበለጠ ጥንካሬ ያስፈልግሀል አለው፡፡” 8 ስለዚህ ተነሥቶ ተጨማሪ ምግብ በላ ውሀም ጠጣ ያን ስለአደረገ ለእግዚአብሔር ወደ ተለየው ወደ ኮሬብ ተራራ አርባ ቀንና ሌሊት ለመጓዝ የሚያስችለው በቂ ብርታት አገኘ፡፡ 9 አንድ ዋሻ ውስጥ ገባና እዚያው አደረ፡፡ በሚቀጥለው ጠዋት እግዚአብሔር “ኤልያስ እዚህ ምን ታደርጋለህ አለው፡፡” 10 እንዲህ በማለት መለሰ “እግዚአብሔር የመላእክት ጌታ ሆይ እኔ በቅናት አገለገልኩህ የእሥራኤል ሕዝብ ግን ከአንተ ጋር የገቡትን ቃል ኪዳን ትተዋል፡፡ መሠዊያዎችህን አፈራረሱ ነቢያትህን ሁሉም ገደሉ፡፡ ያልገደሉት እኔን ብቻ ነው እኔንም ለመግደል በመሞከር ላይ ናቸው፡፡ ስለዚህ ከእነርሱ በመሸሽ ላይ ነኝ” 11 እንዲህ አለው እግዚአብሔር “ውጣና በዚህ ተራራ ላይ በማልፍበት ጊዜ በፊት ለፊቴ ቁም” ኤልያስ እንደታዘዘው አደረገ፡፡ እዚያ ቆሞ እንዳለ ብርቱ አውሎ ንፋስ ተራራውን መታው በተራራው ጎን ዓለቶች ተሰነጣጠቁ፡፡ ነገር ግን በንፋሱ ውስጥ እግዚአብሔር አልነበረም፡፡ ከዚያም መሬት ተንቀጠቀጠ እግዚአብሔር በመሬት መንቀጥቀጡ ውስጥ አልነበረም፡፡ 12 በኋላም እሥት ነደደ ቀጥሎ ዝቅ ያለ የሹክሹክታ ድምፅ ተሰማ 13 ኤልያስ ያን ሲሰማ መጎናፀፊያውን ፊቱ ላይ ጠመጠመ ከዋሻው ወጥቶት መግቢያው ላይ ቆመ፡፡ ከዚያም እግዚአብሔር እንዲህ እያለ ሲያናግረው ሰማ “ኤልያስ እዚህ ምን ታደርጋለህ” 14 እንደገና እንዲህ በማለት መለሰ፡፡ “እግዚአብሔር የመላእክት ሠራዊት አዛዥ ሆይ በቅናት አገልግዬሀለሁ፡፡ የእሥራኤል ሕዝቦች ግን ከአንተ ጋር የገቡትን ቃል ኪዳን ተው፡፡ መሠዊያዎችህን አፈራረሱ ነቢያትህን ሁሉ ገደሉ፡፡ ያልገደሉት እኔን ብቻ ነው፡፡ እናም አሁን ሊገድሉን በመሞከር ላይ ናቸው በመሆኑም ከእርነርሱ በመሸሽ ላይ ነኝ፡፡” 15 ከዚያም እንዲህ በማለት ነገረው “ደማስቆ አቅራቢያ ወደሚገኘው በረሀ ተመለስና ሂድ፡፡ እዚያ ስትደርስ ሐዛኤል የሚባለውን ሰው የወይራ ዘይት ቀባው ከዚያም አራም ንጉሥ እንዲሆን ሹመው፡፡ 16 ከዚያም የኒምሺን ልጅ ዮሀን የእሥራኤል ንጉሥ እንዲሆን ቀባው፡፡ የሣፋጥ ልጅ የሆነው ኤልባዕን ከአቤል ሞኔህ አንተ ከሄድክ በኋላ የኔ ነቢይ እንዲሆን ቀባው፡፡ 17 የሀዛኤል ሠራዊት ብዙ ሰው ይገድላል በእርሱ ሠራዊት ከመግደል ያመለጠ የዮሁ ሠራዊት በዮሁ ሠራዊት ከመገደል የሚያመልጡት በኤልሳ ይገደላሉ፡፡ 18 በአልን ለማምለክ በፍፁም ያላጎነበሱ ወይም የእርሱን ጣኦት ያልሰሙ ሰባት ሺህ ሰዎች መኖራቸውን ማወቅ አለብህ፡፡” 19 ስለዚህ ኤልሳ ወደ አራም በመሄድ ኤልሳን አገነው በሬዎች ጠምዶ ያርስ ነበር፡፡ በዚያው የእርሻ ሥፍራ በሬዎች ጠምደው የሚያርሱ ሌሎች አሥራ አንድ ሰዎች ነበሩ፡፡ ኤልያስ ወደ ኤልሳ በመሄድ የራሱን ኮት አወለቀና ለኤልሳ አለበሰው ኤልያስ ይህን ያደረገው ኤልሳ የእርሱን የነቢይነት ሥፍራ እንዲወስድ መፈለጉን ለኤልሳ ለማሳየት ነው፡፡ ከዚያ ከሥፍራው መሄድ ጀመረ፡፡ 20 ኤልሳ በሬዎቹን እንደቆሙ ተወና በሩጫ ኤልያስን በመከተል እንዲህ አለው “ከአንተ ጋር እሄዳለሁ መጀመሪያ ግን ወላጆቼን ደህና ሁኑ ብዬ በመሳም ልሰናበታቸው” ኤልያስ እንዲህ ብሎ መለሰለት “በጣም ጥሩ ወደቤት ሂድ ነገር ግን ልብሴን ለአንተ የሰጠሁበትን ምክንያት እንዳትረሳ” 21 ስለዚህ ኤልሳ ወደ ቤቱ ተመለሰ፡፡ በሬዎቹን አረደና ሥጋቸውን ቆራረጠ የበሬዎቹን በማንደድም ሥጋውን ለመጥበስ የሚበቃ እሣት አነደደ፡፡ ሥጋውን በከተማው ላሉ ሌሎች ሰዎች አከፋፈለ ሁሉም በሉ፡፡ ከዚያም ከኤልያስ ጋር በመሄድ ረዳቱ ሆነ፡፡