1 ለሦስት ዓመታት ያህል ሠማሪያ ውስጥ ዝናብ አልዘነበም፡፡ እግዚአብሔር ኤልያስን እንዲህ አለው “ሄደህ ከንጉሥ አክአብ ጋር ተገናኝና በቶሎ ዝናብ የማዘንብ መሆኔን ንገረው፡፡” 2 ኤልያስ አክአብን ሊያናግረው ሄደ ሰማሪያ ውስጥ አንድ ሰው እንኳን የሚበላው ምንም ምግብ አልነበረም፡፡ 3 አባድያ የሚባል ሰው እዚያ ነበር፡፡ የንጉሡ ቤተመንግሥት ኃላፊ ነበር እግዚአብሔርንም በጣም ይፈራ ነበር፡፡ 4 በአንድ ወቅት ንግሥት ኤልዛቤል የእግዚአብሔርን ነቢያት ሁሉ ለመቅደል በሞከረች ጊዜ አባድያ መቶዎቹን ሁለት ዋሻዎች ውስጥ ደበቃቸው በእያንዳንዱ ዋሻ ውስጥ አምሳዎቹን በመሸሸግ ምግና ውሃ አመጣላቸው፡፡ 5 በዚህ ጊዜ ሰማርያ ውስጥ ርሀቡ በጣም ተባብሶ ነበር፡፡ በመሆኑም አክአብ አባድያን ጠራና እንዲህ አለው “ፈረሶቼና በቅሎዎቼ በርሀብ እንዳይሞቱ በማንኛውም ምንጭ አካባቢና በማንኛውም ሸለቆ ውስጥ በቂ ሣር እናገኝ እንደሆነ እንፈልግ” 6 እንዲያተባበሉና በአካባቢው ምድር በእግራቸው ይዘዋወሩ ጀመር፡፡ አባድያ ብቻውን ወደ አንድ አቅጣጫ ሄደ አክአብ ደግሞ ብቻውን ወደ ሌላ አቅጣጫ ተጓዘ፡፡ 7 አባድያ በመጓዝ ላይ እያለ ኤልያስ ወደርሱ ሲመጣ ተመለከተ፡፡ አባድያ ኤልያስን አወቀውና እፊተ በመንበርከክ እንዲህ አለ “በእርግጥ ጌታዬ ኤልያስ ነህን” 8 ኤልያስም “አዎ ነኝ አሁን ወደ ጌታህ ወደ አክዓብ ሂድና እዚህ መኖሬን ንገረው አለ፡፡” 9 አባድያ እንዲህ በማለት ተቃወመ “ጌታዬ ሆይ በፍጹም አልበደልኩህም ታዲያ ለመንድነው ወደ አክአብ መልሰህ የምትልከኝ ይገድለኛል 10 ንጉሥ አክአብ በእያንዳንዱ መንግሥት ውስጥ ሁሉ ይፈልግህ ነበር፡፡ የያንዳንዱ መንግሥት ንጉሥ ኤልሳ እዚህ የለም ባለው ቁጥር የዚያ አገር ንጉሥ እውነት መናገሩን በመሀላ እንዲያረጋግጥለት ይጠይቅ ነበር፡፡ የተናገርኩት ሁሉ እውነት መሆኑን አምላክህ እግዚአብሔር ያውቃል፡፡ 11 ነገሩ እንዲህ ሆኖ ሳለ አንተ ሂድና ኤልያስ እዚህ አለ ብለህ ለጌታህ ንገር 12 እንደተለየሁህ ወዲያው የእግዚአብሔር መንፈስ ወስድሀል ወዴት እንደሚወስድህ እኔ አላውቅም ስለዚህ እዚህ መሆንህን ለአካብ ስነግረው ወደ እኔ ቢመጣና እዚህ ባያገኘህ ይገድለኛል ከልጅነቴ ጀምሮ እግዚአብሔር የማመልክ ስለሆንኩ መሞት አይገባኝም፡፡ 13 ጌታዬ ሆይ ኤልዛቤል የእግዚአብሔርን ነቢይት ሁሉ ለመግደል በፈለገች ጊዜ ስለአደረኩት ነገር አልሰማህም አንድ መቶዎቹን ሁለት ዋሻዎች ውስጥ በመደበቅ ምግብና ውሃ አቀርብላቸው ነበር፡፡ 14 አሁን ጌታዬ ኤልያስ እዚህ መኖሩን ሂድና ለጌታህ ንገር ትለኛለህ ያንባደርግና እርሱ መጥቶ ቢያጣህ ይገድለኛል፡፡” 15 ኤልያስ ግን እንዲህ አለ “እግዚአብሔር የመላእክት ሠራዊት አዛዥ እኔ የማገለግለው ዛሬ ከአክአብ ጋር ለመገናኘት እሄዳለሁ ብዬ በአክብሮት ስናገር እውነት በመናገር ላይ መሆኔን ያውቃል፡፡” 16 ስለዚህ ኤልያስ በመምጣቱን ለአክአብ ለመንገር አባድያ ሄደ፡፡ አክአብም ሊገናኘው ሄደ፡፡ 17 ኤልያስን ሲያየው እንዲህ አለ “በእሥራኤል ሕዝብ ላይ ችግር እንዲመጣ የምታደርግ አንተ ነህ፡፡” 18 ኤልያስ እንዲህ በማለት መለሰ “በእሥራኤል ሕዝብ ላይ ችግር እንዲመጣ ያደረግሁት እኔ አይደለሁም ችግር እንዲመጣ ያደረገችሁት አንተና ቤተሰቦችህ ናችሁ የእግዚአብሔርን ትእዛዛት እንታዘዝም አለችሁ፡፡ እና ከእርሱ ይልቅ የበዓልን ጣአቶች አመለካችሁ 19 ስለዚህ አሁን የእሥራኤል ሕዝብ በሙሉ ወደ ቀርሜሎስ ተራራ እንዲመጣ እዘዝ እና በዓልን የሚያመልኩትን 450 እና አሼራ የተባለችውን እና ሚስትህ ኤልዛቤል አብራት ምግብ እንድትበላ የምትጠራትን ጣኦት የሚያመልኩትን አራት መቶ ነቢያት ሁሉ ወደ ሥፍራው ስለመውሰድህ እርግጠኛ ሁን፡፡” 20 ስለዚህም አክዓብ ነቢያቱን ሁሉ እና ሌሎቹን እሥራኤላውያን ሁሉ ወደ ቀርሜ ስስ ተራራ አመጣቸው ኤልያስም ወደዚያ ሄደ፡፡ 21 ከዚያም ኤልያስ በሰፍራው በነበሩት ሰዎች ፊት ቆመና እንዲህ አለ፡ “እውነተኛው አምላክ ማን መሆኑን በተመለከተ እስከመቼ ሳትወስኑ ትኖራላችሁ እግዚአብሔር አምላክ ከሆነ እርሱን አምልኩ፡፡ በአል እውነተኛ አምላክ ከሆነ ደግሞ እርሱን አምልኩ” ሕዝቡ ግን መልስ ከመስጠት ዝም አለ ምክንያቱም እግዚአብሔርን እናመልካለን ቢሉ ኤልዛቤል የምታደርስባቸውን ነገር ፈርተዋል፡፡ 22 ኤልያስ እንዲህ አለ “የቀረሁት እውነተኛው የእግዚአብሔር ነቢይ እኔ ነኝ በዓል ግን 450 ነቢያት አሉት፡፡ 23 ሁለት ኮርማዎችን አምጡ የበዓል ነቢያት የፈለጉትን አንዱን ይመረጡ የመረጡትን ይረዱ ሥጋውን በትንንሹ ይቆራርጡ እና እነርሱ በሠሩት መሠዊያ ላይ በተረበረበው እንጨት ላይ ያድርጉት ነገር ግን ከእንጨቱ በታች እሣት ማንደድ የለባቸውም፡፡ ኮርማ እኔ አርድ እና ሥጋውን ቆራርጩ በምሠራው መሠዊያ ላይ አስቀምጠዋለሁ 24 ከዚያ በኋላ እነርሱ አምላካቸውን መጥራት አለባቸው እኔ ደግሞ እግዚአብሔርን እጠራለሁ መሠዊያው ላይ ባለው እንጨት ላይ በሚነድ እሣት የሚመልስ አምላክ እውነተኛ አምላክ ነው” በዚህ ጊዜ ሰው ሁሉ የኤልያስ አሳብ ጥሩ ነው አሉ፡፡ 25 ከዚያም ኤልያስ ለበዓል ነቢያት እንዲህ አላቸው “በመጀመሪያ እናንተ በዓልን ጥሩ ምክንያቱም እዚህ ያላችሁት ብዙ ናቸው አንዱን ኮርማ ምረጡና አዘጋጁት ከዚያም አምላካችሁን ጥሩ ነገር ግን በእንጨቱ ሥር እሣት እንዳታነዱ” 26 ስለዚህ ከኮርማዎቹ አንዱን አረደው ቆራረጡና ቁርጥራጮቹን መሰዊያው ላይ አደረጓቸው ከዚያም በጠዋቱ ጊዜ በሙሉ በዓልን ጠሩ፡፡ እንዲህ እያሉ ጮሁ በዓል መልሰልን ግን ማንም አልመለሰም በጭራሽ ምንም መለስ አልመጣ ከዚያም በሠሩት መሠዊያ ዙሪያ ሥርዓት በሌለው ሁኔታ ጨፈሩ፡፡ 27 ቀትር ሲሆን ኤልያስ እንዲህ እያለ ይቀልድባቸው ጀመር “በእርግጥ በዓል አምላክ ነው፡፡ በጣም መጮህ የሚያስፈልጋችሁ ይመስላል ምናልባት ስለ አንድ ነገር በማስብ ላይ ይሆናል ምናልባት ወደ መፀደጃ ቤት ሄዷል ወይም ወደ አንድ ሥፍራ በመጓዝ ላይ ነው ምናልባት ተኝቶ ስለሚሆን መቀስቀስ ያስፈልጋችኋል” 28 እነርሱም ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ይጮሁ ጀመር፡፡ ከዚያም በአልን በሚያመልኩበት ጊዜ ሁል ጊዜ ከሚያደርጓቸው ነገሮች አንዱን በማድረግ ሰውነታቸውን በቢለዋና በሰይፍ ብዙ ደም እስኪፈሳቸው ድረስ ይቆራርጡ ጀመር 29 ከቀትር በኋላ በነበረው ጊዜ ሁሉ በአልንመጥራታቸውን ቀጠሉ፡፡ ነገር ግን መልስ የሚሰጥ ድምፅ አልነበረም መልስ የለም፡፡ ትኩረት የሚሰጥ አምላክ አልነበረም፡፡ 30 ከዚያም ኤልያስ ወደዚህ ጠጋበሉ እያለ ሕዝቡን ጠራ እርሱም በዙሪያው ተሰበሰቡ በበአል ነቢያት የፈረሰውን የእግዚአብሔር መሰዊያ አደሰ፡፡ 31 ቀጥሎም አሥራ ሁለት ትልልቅ ድንጋዮች አመጣ እያንዳንዱ አንዱን የእሥራኤል አልነገድ እንዲወክል ነው 32 ስለዚያ ድንጋዮች የእግዚአብሔርን መሠዊያ ሠራ በመሰዊያው ሀያ ሊትር ውሃ ለመያዝ የሚችል ትንሽ ጉድጓድ ቆፈረ፡፡ 33 በድንጋዮቹ ላይ እንጨት ከመረ፡፡ ኮርማውን ገደለና ሥጋውን በትንንሹ ቆራረጠ፡፡ ቁርጥራጩን በእንጨቱ ላይ አደረገ፡፡ ከዚያም እንዲህ አለ “አራት ጋኖችን በውሀ ሙሉና ውሀውን በሥጋውና በእንጨቱ ላይ አፍስሱ” እንደነገራቸው አደረጉ 34 ከዚያም እንዲህ አለ “ያደረጋችሁትን ድገሙ እንደገና አደረጉ፡፡” አሁንም ለሦስተኛ ጊዜ “አድርጉ አለ” እንደገና አደረጉ፡፡ 35 እንዲያ በመደረጉ ውሀው ወደታች ከመሰውያው ፈሰሰና ጉድጓዶቹን ሞላ፡፡ 36 የምሽቱን መስዋዕት የማቅረቢያው ጊዜ ሲደርስ ኤልያስ ወደ መስዊያው ቀረበና ጸለየ እንዲህም አለ “እግዚአብሔር አንተ ቅድመ አያቶቻችን አብርሀም ፣ይስሐቅ እና ያዕቆብ ያመለኩህ አምላካችን ነህ አንተ እሥራኤላውያን ሕዝቦች ሊያመልኩህ የሚገባ አምላክ መሆንህን ዛሬ አረጋግጥ እኔም አግልጋይህ መሆኔን አረጋግጥ፡፡እነዚህን ሁሉ ነገሮች አንተስለነገርከኝ ያደረኳቸው መሆኑንም አረጋግጥ፡፡ 37 እግዚአብሔር ሆይ መልስ ስጠኝ እነዚህ ሰዎች አንተ እግዚአብሔር መሆንህን እና እንደገና በአንተ እንዲያምኑ ያደረካቸው መሆኑን እንድያውቁ መልስ ስጠኝ” 38 ወዲያው ከእግዚአብሔር የሆነ እሣት ከሰማይ ወረደ የተቆራረጠውን ሥጋ፣እንጨቱን ፣ድንጋዮቹን እና በመሰዊያው ዙሪያ ያለውን አፈር አቃጠለ ጉድጉዱ 39 ሕዝቡን በተመለከቱ ጊዜ መሬት ላይ ተደፍተው እንዲህ በማለት ጮሁ “እግዚአብሔር እርሱ አምላክ ነው” 40 ከዚያም ኤልያስ እንዲህ በማለት ትእዛዝ ሰጠ “የበአልን ነቢያት ሁሉ ያዟቸው ማንም እንዳያመልጡዋችሁ” ስለዚህ ሕዝቡ የበአልን ነቢያት ያዟቻና ከተራራው እያወረዱ ወደቂሾን ወንዝ ውስዷቸው እና እዚያ ያሉትን ሁሉ ኤልያስ ገደላቸው፡፡ 41 ከዚያም ኤልያስ እንዲህ አለው ሂድ እህልና ውሀ ቅመስ ነገር ግን በፍጥነት አድርገው ምክንያቱም በአጭር ጊዜ ውስጥ ከባድ ዝናብ ሊዘንብ ነው 42 ከዚያም አክአብ እና ሰዎቹ ብዙ ምግብ ሊያዘጋጁ ሄዱ ኤልያስ ግን ወሰ ቀርጫሎስ ተራራ ጫፍ ተመለሰና ጸለየ፡፡ 43 ከዚያም አገልጋዩን እንዲህ አለው “ሂድና የዝናብ ደመና መኖር አለመኖሩን ለማየት ወደ ባሕሩ አቅጣጫ ተመልከት” አገልጋዩ እንደታዘዘው ሄደ በምልክት ተመለሰና “ምንም አላየሁም አለ” ይህ ለስድስት ጊዜ ተከናወነ 44 አገልጋዩ ለሰባተና ጊዜ ከሄደ በኋላ ግን ተመለሶ መጣና እንዲህ አለ “ከባሕሩ በላይ በጣም ትንሽ ደመና አየሁ፡፡ እጄን ሥዘረጋ የደመናው መጠን መዳፌን ያክላል” ኤልያስ ድምፁን ከፍ አደረገና “ወደ ንጉሥ አክአብ ሂድና ሠረገላውን አዘጋጅቶ ቶሎ ወደ ቤቱ እንዲሄድ ንገረው ያን ካላደረገ ዝናቡ አያስኬደውም አለው፡፡” 45 ወዲያው ሰማዩ በጥቁር ደመና ተሞላ፡፡ ከባድ ንፋስ ነፈሰና ከባድ ዝናብ ይዘንብ ጀመር፡፡ አክዓብ በሠረገላው ሆኖ ኢይዝራኤል መመለስ ጀመረ፡፡ 46 እግዚአብሔር ለኤልያስ እጥፍ ብርታት ሰጠው፡፡ በፍጥነት ለመሮጥ እንዲችል ልብሱን በወገቡ ዙሪያ ጠበቅ አድርጎ በመታጠቅ እስከ ኢይዝራኤል በአክዓብ ሠረገላ ፊት እሮጠ፡፡