ምዕራፍ 1

1 ንጉሥ ዳዊት በጣም በሸመገለ ጊዜ ምንም እንኳን አገልጋዮቹ በምሽት ብዙ የብርድ ልብሶች ቢያለብሱት ልብሱ ሙቀት ሊሰጠው አልቻለም 2 በመሆኑም እንዲህ አሉት ግርማዊ ሆይ ከአንተ ጋር በመሆን የምትንከባከብህ እንዲት ወጣት ልጃገረድ ፈልገን እንድናመጣልህ ፍቀድልን 3 ንጉሡ ፈቀደላቸው፣ ስዚህ አንድት ቆንጆ ወጣት ለማግኘት በመላው እሥራኤል ፈለጉ እናም ሹኔም በምትባል ከተማ ውስጥ አቢሸግ የምትባል ሴትዮ አገኙና ወደንጉሡ አመጧት 4 በእውነት በጣም ቆንጆ ነበረች፣ ንጉሡን ተንከባከበችው ንጉሡ ግን ከእርሷ ጋር የግብረሥጋ ግንኙነት አላደረገም፡፡ 5 - 6 አቤሴሎም ከሞተ በኋላ የዳዊት የበኩር ልጅ የሆነውና ሀጊት ከምትባል ሴት የተወለደው አዶንያስ ሲሆን በጣም ቆንጆ ነበር፡፡ ዳዊት ግን አዶንያስ ያደርግ ስለነበረው ስለማንኛውም ነገር በፍጹም ገልጾት አያውቅም፡፡ አቤሴሎም ከሞተ በኋላ ንጉሥ እሆናለሁ በማለት አስቦ ነበር፡፡ በመሆኑም እንዲህ እያለ ይኩራራ ጀመረ አሁን ንጉሥ እሆናለሁ፡፡ ከዚያም ለራሱ ጥቂት ሠረገላዊችና የሚነዷቸው ሰዎች ሠረገላውን የሚስቡ ፈረሶች እንዲሁም በሚሄድበት ሥፍራ ሁሉ በሠረገላዎች እንደጋሻ ጃግሬዎች የሚሮጡ አምሳ ወንዶች ለራሱ አዘጋጀ፡፡ 7 አንድ ቀን የዳዊት ሠራዊት አዛዥ ከሆነው ከኢዮአብና ከካሕኑ ከአብያተር ጋር ተማከረ እነርሱም አዶንያስን ሊረዱት ቃል ገቡለት 8 ሌሎች የታወቁ ሰዎች ግን እንረዳህም አሉት፡፡ ይህ ወገን ከሕጉ ሳዶቅን የዳዊት የክብር ዘበኞች ተቆጣጣሪ ተቆጣጣሪ የነበረውን በናንያን ነብዩ ናታንን ሹምዔንን ሬኢን እና የዳዊትን ብርቱ ወታደሮች አይጨምርም፡፡ 9 አዶንያስ አንድ ቀን ኤንሮጌል በሚባለውና በኢየሩሳሌም አቅራቢያ ባለው ሥፍራ ወደ አለውይ ዘሔሌት ዓለት ወደተባለው ቦታ ሄደ የሄደበት ምክንያት በጎች ኮርማዎች እና የቀንድ ከብቶችን ለመስዋት ነበር፡፡ ከንጉሥ ዳዊት የተወለዱትን አብዛኛዎቹን ወንድሞቹን ወደሥፍራው እንዲመጡ ጠራቸው፡፡ ይሁዳ የሚገኙትን የንጉሥን ባሥልጣኖች ሁሉ ወደ በዓሉ ሥፍራ ጠራቸው፡፡ 10 ናታንን በናንያን በጣም የታወቁትን የንጉሡን ወታደሮችና ታናሸ ወንድሙን ሰለሞንን ግን አልጠራቸውም 11 ናታን ሰዎቹ የሚያደርጉትን ነገር ተረዳና ወደ ሰለሞን እናት ወደ ቤርሰቤህ ሄደ እንዲህ በማለት ጠየቃት “የሐጊት ልጅ አዶንያስ እራሱን በማንገሥ ላይ መሆኑን አልሰማሽምን ንጉሥ ዳዊትም ስለዚህ ነገር አያውቅም 12 ስለዚህ አራስሽንና ልጆሽን ሰለሞንን ከመግደል ለማዳን ከፈለግሽ ማድረግ የሚገባሽን እንድነግርሽ ፍቀጅልኝ፡፡ 13 በቀጥታ ወደ ምጉሥ ዳዊት ሂጅና እንዲህ በይው ግርማዊ ሆይ ልጄ ስለምን አንተ ስትሞት ተተክቶህ እንደሚነግሥና በዙፋንህ ላይ ተቀምጦ እንደሚመራ በማረጋገጥ ቃል ገብተህልኝ ነበር፡፡ ታዲያ ለምንድነው ሰዎች አዶንያስ አሁን ንጉሥ ነው እያሉ የሚያወሩት 14 እና ቤርሳቤህ አንቺ ከንጉሡ ጋር በመነጋገር ላይ እያለሽ እመጣና ስለአዶንያስ ለእርሱ በመንገር ላይ ያለሽው ነገር እውነት መሆኑን ነግረዋለሁ፡፡” 15 ስለዚህ ቤርሳቤህ ንጉሡን ለማነጋገር ወደ መኝታ ቤቱ ሄደች በጣም ስለአረጀ አቢሻግ ትንከባከበው ነበር፡፡ 16 ቤርሳቤህ በጣም ዝቅ ብላ በንጉሡ ፊት አጎነበሰች ምን ትፈልጊያለሽ? አላት 17 እንዲህ በማለት መለሰችለት ግርማዊ ሆይ አምላካችን ያሕዌ የምትኖረውን በማዳመጥ ለይ መሆኑን እያወቅህ ልጄ ሰለሞን አንተ ከሞትክ በኋላ ንጉሥ እንደሚሆንና በዙፋንህ ላይ እንደሚቀመጥና እንደሚመራ በማረጋገጥ ቃል ገብተህልኝ ነበር 18 አሁን ግን አዶንያስ እራሱን አንግሷል አንተ ስለዚህ ነገር ምንም አታውቅም 19 ብዙ ሀገርማዎች የሰቡ የቀንድ ከብቶችና በጎች ሰውቷል ሌሎች ወንዶች ልጆችህን ወደ ክብረ በዓሉ ጠርቷቸዋል፡፡ ካሕኑን አብያታርንና የጦርህ አዛዥ የሆነውን ኢዮአብንም ጠርቶታል ልጅህን ሰለሞንን ግን አልጠራውም፡፡ 20 ግርማዊ ሆይ አንተ በሞት ከተለየኽን በኋላ ንጉሥ ስለሚሆነው ሰው እንድትነግረው የአሥራኤል ሕዝብ በመጠበቅ ላይ ነው፡፡ 21 ይህን ባታደርግ የሚሆነው ነገር ልጄ ሰለሞንና እኔ አመጸኞች እንደሆንን አድርጎ ሕዝቡ ይቆጥረናል እናም አዶንያስ እንዲነግሥ ባለመርዳታችን ይገድሉናል፡፡ 22 እንዲህ ለንጉሡ በመንገር ላይ እያለች ናታን ወደ ቤተመንግሥቱ መጣ 23 ነቢዩ ናታን መጣ በማት የንጉሡ አገልጋይ ለዳዊት ነገረው ስለዚህ ቤርሳቤትህ ወጣችና ናታን ንጉሡ ወደ አለበት ገብቶ ግንባሩን ወለሉ ላይ በመቸከል ተንበረከከ፡፡ 24 ከዚያም ናታን እንዲህ አለ ግርማዊ ሆይ ከአንተ ለጥቆ አዶንያስ ንጉሥ እንደሚሆን አስታውቀሀልን 25 ይህን ያልኩበት ምክንያት ዛሬ ወደ ኤንሮጌል በመሄድ ብዙ ኮርማዎች የሰቡ የቀንድ ከብቶችና በጎች በመሰዋቱ ነው ሌሎች ልጆችህን ሁሉ የጦሩን አዛዥ ኢዮአብን እና ካሕኑን አቢታርንም ወደ ሥፍራው ጠርቷቸዋል፡፡ ሁሉም ከእርሱ ጋር እየበሉና እየጠጡ ንጉሥ አዶንያስ ረጅም ዕድሜ እንደሚኖረው ተስፋ እና ደርጋለን በማለት ላይ ናቸው 26 እኔን ካሕኑን ሳዶቅን ወይም ሰለሞንን ግን አልጠራንም 27 አንተ ንጉሥ መሆንህ ካበቃ በኋላ እንዲነግሡ ለምትፈልጋቸው ሌሎች ሰዎች ሳያሳውቁ ይህን ማድረግ የሚገባቸው መሆኑን ተናግረሀል 28 ከዚያም ንጉሥ ዳዊት እንዲህ አለ ቤርሳቤህ እንደገና ወዲህ እንድትመጣ ንገራት በዚሁ መሠረት አንድ ሰው ሄዶ መልእክቱን ነገሯትና መጥታ ንጉሡ ፊት ቆመች 29 - 30 ከዚያም ንጉሡ እንዲህ አለ “ሕያው እግዚአብሔር ከመከራዎቼ ሁሉ አድኖኛል፡፡ እኛ እሥራኤላውያን የምናመልከው ሕያው እግዚአብሔር እየሰማ የኔ ንጉሥነት ከበቃ በኋላ ልጅሽ ሰለሞን ንጉሥ እንደሚሆን ቃል ገብቼልሻለሁ፡፡ ከዚህ ቀደም የገባሁልሽን ቃል ዛሬ የማጸና መሆኔን በሕያው አምላክ ስም አረጋግጥልሻለሁ፡፡” 31 ቤርሳቤህ ተንበርክካ ግንባርዋን ወለሉ ላይ በመትክል እንዲህ አለች “ንጉስ ሆይ ለዘላለም እንደምትኖር ተስፋ አደርጋለሁ” 32 ከዚያም ንጉሥ ዳዊት አንድ አገልጋዩን እንዲህ አለው “ካሕኑን ሰዶቆን ነቢዩን ናታንን እና በናንያን ጥራቸው” አገልጋዩም ሄዶ ጠራቸው ተጠሪዎቹ ሲመጡ 33 እንዲህ አላቸው “ልጄን ሰለሞንን በእኔ በቅሎ ላይ አስቀምጡትና ከባለሥልጣኖቼ ጋር ወደ ግዮን ምንጨ ውሰዱት 34 እዚያም እናንተ ሁለታችሁ ሳዶቅና ናታን የእሥራኤል ንጉሥ እንዲሆን የወይራ ዘይት ቀቡት ከዚያም ሁለታችሁ መለኮትን ያኔ ሕዝቡ ሁሉ ንጉሥ ሰለሞን ለብዙ ዓመታት ይኑር ብሎ ይጩህ 35 ከዚያም አጅባችሁ ወዲህ ኑ መጥቶ በዙፋኔ ላይ ይቀመጣል በእኔ ምትክ ንጉሥ የሆናል የእሥራኤልና የየሁዳ ሕዝብ ሁሉ መሪ እንዲሆን ሾሜዋለሁ” 36 በናያም እንዲህ በማለት መለሰ “ያዘዝከንን እናደርጋለን የእናንተና የእኛ አምላክ የሆነው ዘላለማዊ አምላክ የተባለው እንዲፈጸም እንደሚያደርግ እናምናለን 37 ንጉሥ ዳዊት ሆይ ዘላለማዊው አምላክ ረድቶሀል ሰለሞንንም ከአንተ ይልቅ ታላቅ ንጉሥ እንዲሆን እንደሚረዳው እናምናለን” 38 ለዚህ ሳዶቅ በናያና የንጉሡ የክብር ዘበኞች የሆኑ ሁለት ቡድን ሰዎች ሄደው ሰለሞንን ንጉሡ በቅሎ ላይ በማስቀመጥ አጀበው ወደ ግዮን ምንጭ ወሰዱት 39 እዚያም ሳዶቅ የወይራ ዘይት የነበረበትን ዕቃ ከተቀደሰው ድንኳን ውስጥ በመውሰድ ሰለሞንን ቀባው ሁለቱ መለኮቱን ነፉ ሕዝቡም በሙሉ እንዲህ እያሉ ጮሁ “ንጉሥ ሰለሞን ለብዙ ዓመታት ይኑር” 40 ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ በደስታ እየጮሁና እምቢልታ እየነፉ አጀበውት ወደ ከተማው ሄዱ ምድሩ እስኪናወጥ ድረስ ድምጻቸው ከፍ አድርገው ጮሁ፡፡ 41 አዶንያስና የጠራቸው እንግዳዎቹ በበዓሉ ሥፍራ ግብዣቸውን በማብቃት ላይ እንዳሉ ድምጹን ሰሙ ኢዮአብ የመለከቶቹን በሰማ ጊዜ “ከተማው ውስጥ የሚሳመው ድምፅ ሁሉ ትርጉም ምንድነው” አለና ጠየቀ 42 ገና በመናገር ላይ እንዳለ የካሕኑ የአቢያተር ልጅ ዮናታን በሥፍራው ደረሰ አዶንያስ እንዲህ አለ “ግባ ልናምነው የምንችለው ሰው አንተነህ ይዘኽው የመጣኸው መልካም ዜና መሆን አለበት፡፡” 43 ዮናታን እንዲህ በማለት መለሰ “አይደለም መልካም ዜና የለኝም ታላቁ ንጉሥ ዳዊት ሰለሞንን ንጉሥ አደረገው 44 አጅበውት እንዲመጡም ሳዶቅና ናታንን በናንያንና የራሱን ጠባቂዊች ቡድን ወደዚያ ልኳል ሰለሞንን በንጉሥ በቅሎ ላይ ነው ያስቀመጡት 45 ወደ ግዮን ምንጭ ሄዱና እዚያ ሳዶቅና ናታን ንጉሥ እንዲሆን ቀቡት አሁን በደስታ እየጮሁ ከዚያ ወደ ከተማው ተመልሰዋል፡፡ የምታደምጡት ድምጽ እዚያ የሚሰማው ለዚህ ነው፡፡ 46 ስለዚህ አሁን ሰለሞን ንጉሣችን ነው፡፡ 47 በተጨማሪም የቤተመንግሥቱ ባለሥልጣኖች ያደረገውን ማፅደቃቸውን ሊነግሩት ወደ ንጉሥ ዳዊት መጥተዋል፡፡ ለንጉሡም እንዲህ ብለውታል እግዚአብሔር ሰለሞንን አንተ ከሆንከው ይበልጥ ታውቂ ያድርገው ከአንተ የተሻለ እንዲሆን ያድርገው ይህን በሚሉበት ጊዜ ንጉሡ አልጋው ላይ እንደተኛ እግዚአብሔር አምላክን በማምለክ እራሡን ጎንበስ አድርጓል 48 ከዚያም እንዲህ አለ እኛ አሥራኤላውያን የምናመልከውን ሕያው እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፡፡ ምክንያቱም ዛሬ ከልጆቼ አንዱ ንጉሥ እንዲሆን ፈቅዷል፡፡ ይህ ሲከናወን እንድመለከትም ፈቅዶልኛል፡፡” 49 በዚህ ጊዜ የአዶንያስ እንግዶች ሁሉ ተንቀጠቀጡ ወዲያው ብድግ በማለት ተበታተኑ 50 አዶንያስ ባደረገው ነገር ምክንያት ሰለሞን የሚያደርስበትን ነገር አስቦ ፈራ ወደ ተቀደሰው ድንኳን ገብቶም የመሰዊያውን ቀንዶች በመሰዊያው ማዕዘን እንዳሉ ያዛቸው ምክንያቱም እንዲያ በሚያደርግበት ጊዜ ማንም እንደማይገድለው አስቧል 51 ነገር ግን አንድ ሰው ለሰለሞን እንዲህ በማለት ነገረው “አየህ አዶንያስ ፈርቶሀል ስለዚህ ወደ ተቀደሰው ድንኳን ሄዶ መሰዊያውን ይዟል፡፡ ከዚህ ሥፍራ ከመውጣቴ በፊት ንጉሥ ሰለሞን እንዲገደል ትእዛዝ የማይሰጥ ስለመሆኑ በሞገሱ ቃል እንዲገባልኝ ፈልጋለሁ በማለት ላይ ነው፡፡” 52 ሰለሞን እንዲህ አለ “ለእኔ ታማኝ መሆኑን ካረጋገጠልኝ በፍፁም አልጎዳውም ስህተት የሆነ ነገር ቢፈጽም ግን ይገደላል” 53 በዚሁ መሠረት ንጉሥ ሰለሞን ጥቂት ሰዎች ወደ አዶንያስ ላከና ከመሠዊያው ሥፍራ አመጡት ወደ ሰለሞን መጣና በፊቱ ሰገደ ሰለሞንም ወደቤትህ ሂድ አለው