ምዕራፍ 1

1 እኔ፣ዮሐንስ ምንም ነገር መኖር ከመጀመሩ አስቀድሞ ስለነበረው እጽፍላችኋለሁ! እኛ ሐዋርያት እርሱ ሲያስተምር ሰምተነዋል! አይተነዋል! እኛ ራሳችን እርሱን አይነተናል ነክተነዋልም! ስለ ዘለዓለማዊ ህይወት ያለውን መልዕክት ያስተማረን እርሱ ነው፡፡ 2 (እርሱ ወደዚህ ወደ ምድር ስለመጣና እኛ ስላየነው፣ ለእናንተ በግልጽ የምንሰብከው ከዘለዓለም የነበረውንና ያየነውን ነው፡፡ እርሱ አስቀድሞ በሰማይ ከአባቱ ጋር ነበር፣ ነገር ግን በእኛ መሃል ለመኖር መጣ፡፡) 3 ከእኛ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ፣ ስለ ኢየሱስ ሲናገር የሰማነውን መልእክት እንሰብካችኋለን፡፡ ህብረታችን ከአባታችን ከእግዚአብሔርና ከልጁ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው፡፡ 4 ስለ እነዚህ ነገሮች የምጽፍላችሁ እውነት እንደሆነ ታውቁ ዘንድ ነው፤ ደግሞም በውጤቱ ሙሉ ለሙሉ ደስተኞች እንሆናለን፡፡ 5 ከእግዚአብሔር የሰማነውና ለእናንተ የምንነግራችሁ መልእክት ይህ ነው፡ እርሱ በፍጹም ኃጢአት አላደረገም፡፡ እርሱ ጨለማ እንደሌለበት ፍጹም አንጸባራቂ ብርሃን ነው፡፡ 6 ከእግዚአብሔር ጋር ህብረት አለን የምንል ከሆነ፣ ነገር ግን ህይወታችንን ባልጸዳ ሁኔታ ከመራን፣ ይህ በክፉ ጨለማ ውስጥ እንደ መኖር ነው፡፡ እንዲህ ካደረግን እየዋሸን ነው፡፡ ህይወታችንን በእግዚአብሔር እውነተኛ መልዕክት እየመራን አይደለም ማለት ነው፡፡ 7 ነገር ግን እግዚአብሔር በሁሉም መንገድ ንጹህ ሆኖ እንደሚኖር በንጽህና መኖር በእግዚአብሔር ብርሃን እንደ መኖር ነው፡፡ ይህን ካደረግን፣ እርስ በእርሳችን ህብረት ይኖረናል፤ ኢየሱስ ለእኛ ሰለሞተም እግዚአብሔር ይቅር ይለናል፤ ይቀበለናልም፡፡ 8 ኃጢአት ሰርተን አናውቅም የሚሉ ራሳቸውን ያስታሉ፤ ደግሞም እግዚአብሔር ስለ እነርሱ የተናገረውን ለማመን ይቃመዋሉ፡፡ 9 ነገር ግን እግዚአብሔር ሁሉጊዜም የተናገረውን ያደርጋል፣ ደግሞም እርሱ የሚያደርገው ሁልጊዜም ትክክል ነው፡፡ ስለዚህ ኃጢአት እንደሰራን ለእርሱ ብንናዘዝ፣ ኃጢአታችንን ይቅር ይላል ደግሞም በሰራነው በደል ሁሉ ከሚሰማን ጥፋተኝነት ነጻ ያደርገናል፡፡ በዚህ ምክንያት፣ ኃጢአት እንደሰራን ለእርሱ መናዘዝ አለብን፡፡ 10 እግዚአብሔር ሁሉም ኃጢአት ሰርተዋል ስላለ፣ ፈጽሞ ኃጢአት አልሰራንም የሚሉ እግዚአብሔር ይዋሻል ብለው መናገራቸው ነው! እግዚአብሔር ስለ እኛ የተናገረውን አልተቀበሉም ማለት ነው!