ምዕራፍ 1

1 2 3 4 1 እግዚአብሔር የፈጠረው የመጀመሪያ ሰው አዳም ነበር፡፡ የአዳም ልጅ ሴት ነበር፡፡ የሴት ልጅ ሄኖክ ነበር፡፡ የሄኖክ ልጅ ቃይናን ነበር፡፡ 2 የቃይናን ልጅ መላልኤል ነበር፡፡ የመላልኤል ልጅ ያሬድ ነበር፡፡ የያሬድ ልጅ ሄኖክ ነበር፡፡ 3 የሄኖክ ልጅ ማቱሳላ ነበር፡፡ የማቱሳላ ልጅ ላማሕ ነበር፡፡ የላሜሕ ልጅ ኖኅ ነበር፡፡ 4 የኖኅ ወንዶች ልጆች ሴም፣ ካም እና ያፌት ናቸው፡፡ 17 18 19 17 የሴም ወንዶች ልጆች ዑፅ፣ ሁል፣ ጌቴር እና ሞሳሕ ናቸው፡፡ 18 አርፋክሰድ ሰላን ወለደ፣ ሰላም ዔቦርን ወለደ፡፡ 19 ዔቦር ሁለት ወንዶች ልጆች ወለደ፤ የአንደኛው ስም ፋሌቅ ነበር፤ ፋሌቅ፣ ‹‹መከፈል›› ማለት ሲሆን፣ እንዲህ የተባለው እርሱ በነበረበት ዘመን በምድር የሚኖሩ ሰዎች በተለያየ ቋንቋ በመከፈላቸው ነበር፡፡ የፋሌቅ ታናሽ ወንድም ዮቅጣን ነበር፡፡ 20 21 22 23 20 ዮቅጣን አልሞዳድን፣ ሣሊፍን፣ ሐስረሞትን፣ ያራሕን፣ 21 ሁደራምን፣ አውዛልን፣ ደቅሳን 22 ዖባልን፣ አቢሚኤልን፣ ሳባን፣ 23 አፊርን፣ ኤውላጥን፣ ዮባብን ወለደ፡፡ 24 25 26 27 24 ሴም፣ አርፋክስድን፣ ሰለን፣ 25 ዔቦርን፣ ፋሌቅን ራግውን 26 ሴሮሕን፣ ናኮርን፣ ታራን፣ 27 እንዲሁም በኃላ አብርሃም የተባለው አብራምን ወለደ፡፡ 28 29 30 31 28 የአብርሃም ወንዶች ልጆ ይስሐቅና እስማኤል ናቸው፡፡ 29 እስማኤል አብርሃም ከአገልጋዩ ከአጋር የወለደው ነው፡፡ ዐሥራ ሁለቱ የእስማኤል ወንዶች ልጆች የበኩር ልጁ ነባዮት፣ ቄዳር፣ ነብ፣ ዳንኤል፣ መብሳም፣ 30 ማስማዕ፣ ዱማ፣ ማሣ፣ ኩዳን፣ ቴማን፣ 31 ኢጡር፣ ናፌስ እና ቄድማ ናቸው፡፡ 32 33 32 የአብርሃም ሚስት ሣራ ከሞተች በኃላ፣ ኬጡራ የምትባል ሌላ ሚስት አገባ፡፡ ከእርሷ የተወለዱ ወንዶች ልጆች ዘምራን፤ ዮቅሳን፣ ሜዳን፣ ምድያም የስቦቅና ስዌሕ ናቸው፡፡ የዮቅሳን ወንዶች ልጆች ሳባ እና ድዳን ናቸው፡፡ 33 የምድያም ወንዶች ልጆች ጌፌር፣ ዔፌር፣ ሄኖኅ፣ አቢዳዕ፣ ኤልዳዓ ናቸው፡፡ 38 39 40 38 ሌላው የዔሳው ወንድ ልጅ ሴይር ነው፡፡ የሴይር ልጆች በኤዶም አካባቢ ይኖሩ ነበር፡፡ የእርሱ ወንዶች ልጆች ሎጣን፣ ሦባል፣ ድብዖን፣ ዓና፣ ዲሶን፣ ኤጽር፣ እና ዲሳን ናቸው፡፡ 39 የሎጣን ወንዶች ልጆች ሖሪ እና ሄማም ሲሆኑ፣ የሎጣን እኅት ቲሞናዕ ነበረች፡፡ 40 የሦባል ወንዶች ልጆች ዔልዋን፣ ማኔሐት፣ ዔባል፣ ስፎ እና አውናም ናቸው፡፡ 41 42 41. የዓና ወንድ ልጅ ዲሶን ነበር፡፡ የዲሶን ወንዶች ልጆች ሔምዳን፣ ኤስባን፣ ይትራን እና ክራን ናቸው፡፡ 42 የኤጽር ወንዶች ልጆች ቢልሐን፣ ዛሪዋንና ዓቃን ናቸው፡፡ 46 47 48 46 ሑሳም ሲሞት የቤዳድ ልጅ ሐዳድ በእግሩ ተተክቶ በዓዊት ነገሠ፡፡ የሐዳድ ሰራዊት ሞዓብ አካባቢ የነበረውን የምድያም ጦር ድል አደረገ፡፡ 47 ሐዳድ ሲሞ የመሥሬቃ ሰው የሆነው ሠምላ በእግሩ ተተክቶ ነገሠ፡፡ 48 ሠምላ ሲሞት በወንዙ አጠገብ ያለችው የርኆቦት ሰው የሆነው ሳኡል በእግሩ ተተክቶ ነገሠ፡፡ 51 52 53 54 51 ሀዳድም ሞተ፡፡ ዋና ዋናዎቹ የኤዶም ሕዝብ አለቆች እነዚህ ነበሩ፤ ቲምናዕ፣ ዓልዋ፣ ዮቴት፣ አህሊባማ፣ ኤላ፣ ራኖን፣ 53 ቄኔዝ፣ ቴማን፣ ሚብሳር፣ 54 መግዲኤል፣ እና ዒራም፡፡