Genesis 37
Genesis 37:1
ያዕቆብ ለመኖር የተቀመጠው የት ነበር?
ያዕቆብ በከነዓን ምድር ኖረ
ዮሴፍ ከወንዶሞቹ ጋር በጎች በሚጠብቅበት ወቅት ወደ አባቱ ያመጣው ምን ነበር?
ዮሴፍ የወንድሞቹን የክፋታቸውን ወሬ ወደ አባታቸው አመጣ
Genesis 37:3
እስራኤል ከወንድሞቹ ይልቅ ዮሴፍን መውደዱን ያሳየው እንዴት ነበር?
እስራኤል ለዮሴፍ ያጌጠ እጀ ጠባብ ሠራለት
የዮሴፍ ወንድሞች ስለ ዮሴፍ ምን አሰቡ?
የዯሴፍ ወንድሞች ጠሉት፣ በሰላም ሊያናግሩትም አልቻሉም
Genesis 37:7
ዮሴፍ በመጀመሪያው ሕልሙ ምን አየ?
ዮሴፍ የእርሱ ነዶ ሲቆምና የወንድሞቹ ነዶዎች ለእርሱ ነዶ ሲሰግዱ አየ
ዮሴፍ ስለ መጀመሪያ ሕልሙ ከነገራቸው በኋላ የዮሴፍ ወንድሞች ስለ ዮሴፍ ምን አሰቡ?
የዮሴፍ ወንድሞች በይበልጥ ጠሉት
ዮሴፍ በሁለተኛው ሕልሙ ምን አየ?
ዮሴፍ፣ ፀሐይ፣ ጨረቃና አሥራ አንድ ከዋክብት ለእርሱ ሲሰግዱለት አየ
Genesis 37:9
በዮሴፍ ሕልም ውስጥ ፀሐይ፣ ጨረቃና ከዋክብቱ የሚወክሉት ምንን ነበር?
ፀሐይ፣ ጨረቃና ከዋክብቱ የሚወክሉት የዮሴፍን አባት፣ እናትና ወንድሞቹን ነበር
Genesis 37:12
ያዕቆብ ዮሴፍን ከኬብሮን ሸለቆ የላከው ምን እንዲያደርግ ነበር?
ያዕቆብ፣ የወንድሞቹን ደህና መሆን እንዲያይና ወሬአቸውን እንዲያመጣለት ዮሴፍን ከኬብሮን ሸለቆ ላከው
Genesis 37:18
የዮሴፍ ወንድሞች ዮሴፍ ሲመጣ ባዩት ጊዜ ምን ለማድረግ ዐቀዱ?
የዮሴፍ ወንድሞች ዮሴፍን ለመግደልና ከጉድጓዶቹ በአንዱ ውስጥ ሊጥሉት ዐቀዱ
Genesis 37:21
ሮቤል ለወንድሞቹ ያቀረበው አሳብ ምን ነበር? ለምን?
ሮቤል በኋላ ይታደገው ዘንድ ወንድሞቹ በጉድጓድ ውስጥ ብቻ እንዲጥሉት አሳብ አቀረበ
Genesis 37:27
የዮሴፍ ወንድሞች ዮሴፍን ለማን ሸጡት? በምን ያህል?
የዮሴፍ ወንድሞች ዮሴፍን ለእስማኤላውያን በሃያ ብር ሸጡት
ዮሴፍ የተወሰደው ወዴት ነበር?
ዮሴፍ ወደ ግብፅ ተወሰደ
Genesis 37:31
የዮሴፍ ወንድሞች ዮሴፍ የሞተ ለማስመሰል ምን አደረጉ?
የዮሴፍ ወንድሞች ፍየል በማረድ የዮሴፍን ልብስ በደሙ ውስጥ ነከሩትና ለያዕቆብ ሰጡት
የዮሴፍ ወንድሞች ዮሴፍ የሞተ ለማስመሰል ምን አደረጉ?
የዮሴፍ ወንድሞች ፍየል በማረድ የዮሴፍን ልብስ በደሙ ውስጥ ነከሩትና ለያዕቆብ ሰጡት
Genesis 37:34
ዮሴፍ ሞቷል ብሎ ከደመደመ በኋላ ያዕቆብ ምን አደረገ?
ያዕቆብ ልብሱን ቀደደ፣ ማቅ ለብሶም ለልጁ ብዙ ቀን አለቀሰ
በግብፅ አገር ዮሴፍ የተሸጠው ለማን ነበር?
ዮሴፍ በግብፅ አገር የፈርዖን ሹም ለሆነው ለጲጥፋራ ተሸጠ