Genesis 26
Genesis 26:2
ይስሐቅ የፍልስጥኤማውያን ንጉሥ አቢሜሌክ ወደሚኖርበት ወደ ጌራራ የሄደው ለምን ነበር?
በምድሪቱ ረሃብ ስለ ነበረ ይስሐቅ ወደ ጌራራ ሄደ
ይስሐቅ ወደ ጌራራ ከመሄዱ በፊት እግዚአብሔር አምላክ ምን ነግሮት ነበር?
እግዚአብሔር አምላክ፣ ይስሐቅ ወደ ግብፅ እንዳይሄድና እርሱ እስኪነግረው ድረስ በምድሪቱ እንዲቆይ ነግሮት ነበር
Genesis 26:4
እግዚአብሔር አምላክ ለአባቱ ለአብርሃም ስለ ማለለት መሐላ ለይስሐቅ የነገረው ምንድነው?
እግዚአብሔር አምላክ ለአብርሃም የማለለትን መሐላ ለይስሐቅ እንደሚፈጽምለት ነገረው
Genesis 26:6
እግዚአብሔር አምላክ ይህንን እንደሚያደርግ የተናገረው ለምንድነው?
እግዚአብሔር አምላክ ይህንን እንደሚያደርግ የተናገረው አብርሃም ድምፁን ስለታዘዘና ፍርዱን፣ ትዕዛዙን፣ ሥርዓቱንና ሕጉን ስለ ጠበቀ ነው
ይስሐቅ ስለ ሚስቱ ስለ ርብቃ ለጌራራ ሰዎች ምን አላቸው?
ርብቃ እህቱ መሆኗን ይስሐቅ ለጌራራ ሰዎች ነገራቸው
Genesis 26:9
እንደ አቢሜሌክ አነጋገር፣ በይስሐቅ ውሸት ምክንያት በሕዝቡ ላይ ሊመጣባቸው የነበረው ኃጢአት ምንድነው?
በይስሐቅ ውሸት ምክንያት አንድ ሰው ከርብቃ ጋር ሊተኛና በሕዝቡ ላይ ኃጢአት ሊያመጣ ነበር
እንደ አቢሜሌክ አነጋገር፣ በይስሐቅ ውሸት ምክንያት በሕዝቡ ላይ ሊመጣባቸው የነበረው ኃጢአት ምንድነው?
በይስሐቅ ውሸት ምክንያት አንድ ሰው ከርብቃ ጋር ሊተኛና በሕዝቡ ላይ ኃጢአት ሊያመጣ ነበር
Genesis 26:12
አቢሜሌክ ስለ ርብቃ ምን ትዕዛዝ ሰጠ?
ርብቃን የሚነካ ማንም ቢሆን እንዲገደል አቢሜሌክ ትዕዛዝ ሰጠ
Genesis 26:15
ይስሐቅ ፍልስጥኤምን ለቆ እንዲሄድለት አቢሜሌክ ሲጠይቀው ያቀረበው ምክንያት ምን ነበር?
አቢሜሌክ፣ ይስሐቅ ፍልስጥኤምን ለቆ እንዲሄድለት ጠየቀው፣ ምክንያቱም "...ከእኛ ይልቅ እጅግ በርትተሃልና" አለው
Genesis 26:18
ይስሐቅ በአብርሃም ዘመን ተቆፍረው የነበሩትን የውሃ ጉድጓዶች መቆፈር ለምን አስፈለገው?
በአብርሃም ዘመን ተቆፍረው የነበሩትን የውሃ ጉድጓዶች ይስሐቅ መቆፈር ነበረበት፣ ምክንያቱም አብርሃም ከሞተ በኋላ ፍልስጥኤማውያን አስቁመዋቸው ነበር
Genesis 26:21
የጌራራ እረኞች ያልተጣሉበትን ጉድጓድ ይስሐቅ ምን ብሎ ጠራው?
ይስሐቅ የጌራራ እረኞች ከእርሱ ጋር ያልተጣሉበትን ጉድጓድ ርኆቦት ብሎ ጠራው?
Genesis 26:23
እግዚአብሔር አምላክ በቤርሳቤህ ለይስሐቅ በተገለጠለት ጊዜ እንደ ገና ያጸናለት ምን ነበር?
እግዚአብሔር አምላክ እንደሚባርከውና ዘሩን እንደሚያበዛለት እንደ ገና አጸናለት
እግዚአብሔር አምላክ በቤርሳቤህ ለይስሐቅ በተገለጠለት ጊዜ እንደ ገና ያጸናለት ምን ነበር?
እግዚአብሔር አምላክ እንደሚባርከውና ዘሩን እንደሚያበዛለት እንደ ገና አጸናለት
Genesis 26:28
አቢሜሌክ ከይስሐቅ ጋር ለማድረግ የፈለገው ምን ዓይነት ቃል ኪዳን ነበር? ለምን?
እግዚአብሔር አምላክ ከይስሐቅ ጋር እንደሆነ ስላየ አቢሜሌክ፣ እርስ በእርሳቸው እንዳይጎዳዱ ቃል ኪዳን ለማድረግ ፈለገ
አቢሜሌክ ከይስሐቅ ጋር ለማድረግ የፈለገው ምን ዓይነት ቃል ኪዳን ነበር? ለምን?
እግዚአብሔር አምላክ ከይስሐቅ ጋር እንደሆነ ስላየ አቢሜሌክ፣ እርስ በእርሳቸው እንዳይጎዳዱ ቃል ኪዳን ለማድረግ ፈለገ
Genesis 26:30
አቢሜሌክ በመካከላቸው ቃል ኪዳን እንዲደረግ ላቀረበው ጥያቄ የይስሐቅ ምላሽ ምን ነበር?
ይስሐቅ ማዕድ አቀረበላቸው፣ እርስ በርሳቸውም ተማማሉ
አቢሜሌክ በመካከላቸው ቃል ኪዳን እንዲደረግ ላቀረበው ጥያቄ የይስሐቅ ምላሽ ምን ነበር?
ይስሐቅ ማዕድ አቀረበላቸው፣ እርስ በርሳቸውም ተማማሉ
Genesis 26:34
የኤሳው ሁለት ሚስቶች ከየትኛው የሕዝብ ወገን ነበሩ?
ሁለቱ የኤሳው ሚስቶች ኬጢያውያን ነበሩ
የኤሳው ሚስቶች ከይስሐቅና ከርብቃ ጋር የነበራቸው ግንኙነት ምን ይመስላል?
የኤሳው ሚስቶች ይስሐቅንና ርብቃን ያሳዝኑ ነበር