Genesis 19
Genesis 19:1
ሁለቱ መላእክት ወደ ሰዶም ሲመጡ ሎጥ ባየ ጊዜ ምን አሳብ አቀረበላቸው?
ሌሊቱን በእርሱ ቤት እንዲያድሩና ሲነጋ እንዲሄዱ አሳብ አቀረበላቸው
መላእክቱ ለሎጥ ምን መለሱለት?
መላእክቱ ሌሊቱን በከተማይቱ አደባባይ እንደሚያሳልፉ ተናገሩ
Genesis 19:4
በሎጥ ጉትጎታ፣ መላእክቱ በመጨረሻ ሌሊቱን የት ለማሳለፍ ወሰኑ?
በመጨረሻም፣ መላእክቱ ሌሊቱን በዚያ ለማሳለፍ ከሎጥ ጋር ወደ እርሱ ቤት ሄዱ
የሎጥን ቤት የከበቡት የከተማይቱ ወንዶች የፈለጉት ሎጥ ምን እንዲያደርግ ነበር?
ሰዎቹ ከእነርሱ ጋር መተኛት ይችሉ ዘንድ ሊጎበኙት የመጡትን ሁለት ሰዎች ሎጥ እንዲያወጣላቸው ፈለጉ
Genesis 19:6
ሎጥ ከዚህ ይልቅ ለከተማይቱ ወንዶች ምን አሳብ አቀረበላቸው?
ሎጥ ከሁለቱ ጎብኚዎቹ ይልቅ ሁለቱን ሴቶች ልጆቹን ለከተማይቱ ወንዶች አቀረበላቸው
Genesis 19:9
ሎጥ ላቀረበላቸው የወንዶቹ ምላሽ ምን ነበር?
ሰዎቹ ሎጥ ወዲያ እንዲሄድላቸው ነገሩት፣ በሩን ለመስበርም ቀረቡ
Genesis 19:10
ከዚያ መላእክቱ ምን አደረጉ?
መላእክቱ ሎጥን ወደ ቤት ውስጥ ሳቡትና በውጭ የነበሩትን ወንዶች ዓይኖቻቸውን አሳወሯቸው
Genesis 19:12
መላእክቱ የተናገሩት በእግዚአብሔር አምላክ የተላኩት ምን ለማድረግ መሆኑን ነበር?
መላእክቱ ከተማይቱን ለማጥፋት የተላኩ መሆናቸውን ተናገሩ
Genesis 19:14
ሎጥ ከተማይቱ ልትጠፋ ስለሆነ በአስቸኳይ ከሰዶም እንዲወጡ ለአማቾቹ በነገራቸው ጊዜ ምላሻቸው ምን ነበር?
አማቾቹ ሎጥ የሚቀልድ መሰላቸው
ጎህ በቀደደ ጊዜ መላእክቱ ለሎጥ የነገሩት ምን እንዲያደርግ ነበር?
ሎጥ ሚስቱንና ሴቶች ልጆቹን ይዞ ከከተማይቱ እንዲወጣ መላእክቱ ነገሩት
Genesis 19:16
ሎጥ በዘገየ ጊዜ መላእክቱ የሎጥንና የቤተሰቡን እጆቻቸውን ይዘው ከከተማይቱ ያስወጧቸው ለምን ነበር?
መላእክቱ ከከተማይቱ ውጪ አውጥተው ያስቀመጧቸው እግዚአብሔር አምላክ ስላዘነላቸው ነበር
Genesis 19:18
ከከተማይቱ ውጪ በነበሩበት ጊዜ መላእክቱ ለሎጥ ምን ዓይነት መመሪያ ሰጡት?
ሎጥና ቤተሰቡ ነፍሳቸውን ለማዳን እንዲሸሹና ወደ ኋላቸው እንዳይመለከቱ መላእክቱ ነገሯቸው
Genesis 19:21
መላእክቱ ለሎጥና ለቤተሰቡ የፈቀዱላቸው ወዴት እንዲሸሹ ነበር?
ሎጥና ቤተሰቡ ዞዓር ተብላ ወደምትጠራ ትንሽ ከተማ እንዲሸሹ ተፈቅዶላቸው ነበር
Genesis 19:23
ሎጥ ወደ ዞዓር በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር አምላክ ምን አደረገ?
እግዚአብሔር አምላክ በሰዶምና ገሞራ ላይ ከሰማይ እሳትና ዲን አዘነበባቸው
Genesis 19:26
የሎጥ ሚስት ምን አደረገች? ምንስ ደረሰባት?
የሎጥ ሚስት ወደኋላዋ ተመለከተች፣ የጨው ዓምድም ሆነች
Genesis 19:29
አብርሃም በማለዳ ሜዳማውን አገር ሁሉ ቁልቁል ሲመለከት ምን አየ?
እንደ እቶን ያለ ጢስ ከምድር ወደ ላይ ሲወጣ አየ
Genesis 19:30
ሎጥ ከዚያ ወዴት ሄደ? ለምን?
ሎጥ በዞዓር ለመቀመጥ ስለ ፈራ ከዚያ ተነሥቶ ወደ ተራሮች ሄደ
Genesis 19:31
የሎጥ ሴቶች ልጆች አባታቸውን የሚያካትት ምን ዕቅድ አወጡ?
የሎጥ ሴቶች ልጆች አባታቸውን ለማስከርና ልጆች ይኖሩት ዘንድ ከእርሱ ጋር ለመተኛት አቀዱ
Genesis 19:36
የሎጥ ሴቶች ልጆች አባታቸውን የሚያካትት ምን ዕቅድ አወጡ?
የሎጥ ሴቶች ልጆች አባታቸውን ለማስከርና ልጆች ይኖሩት ዘንድ ከእርሱ ጋር ለመተኛት አቀዱ
ከሎጥ ሴቶች ልጆች የትኞቹ ሁለት የሰዎች ክፍሎች ተገኙ?
ሞዓባውያንና አሞናውያን ሰዎች ከሎጥ ሴቶች ልጆች ተገኙ
ከሎጥ ሴቶች ልጆች የትኞቹ ሁለት የሰዎች ክፍሎች ተገኙ??
ሞዓባውያንና አሞናውያን ሰዎች ከሎጥ ሴቶች ልጆች ተገኙ