Genesis 37

Genesis 37:1

አባቱ በቆየበት አገር በከነዓን ምድር ተቀመጠ

አባቱ በኖረበት በከነዓን ምድር ተቀመጠ

የያዕቆብ ትውልድ ታሪክ ይህ ነው

ይህ ዐረፍተ ነገር በዘፍጥረት 37: 1-5ዐ:26 ያለውን የያዕቆብን ትውልድ ያስታውቃል፡፡ እዚህ ያዕቆብ መላው በተሰቡን ይወክላል፡፡ አት “ይህ የያዕቆብ ቤተሰብ ታሪክ ነው” (ክፍልን እንደሙሉና ሙሉን እንደክፍል የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)

አሥራ ሰባት ዓመት ዕድሜ

17 ዓመት ዕድሜ

ባላ

ይህ የራሔል ሴት አገልጋይ ስም ነው:: በዘፍጥረት 29: 29 ይህን ስም እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)

ዘለፋ

ይህ የልያ ሴት አገልጋይ ስም ነው:: በዘፍጥረት 29: 24 ይህን ስም እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)

ሚስቶች

እነዚህ ሴቶች ልጅ እንዲወልዱ ዘንድ ለያዕቆብ የተሰጡ የልያና የራሔል አገልጋዮች ናቸው

ስለእነርሱ መጥፎ ወሬ

ስለወንድሞቹ መጥፎ ወሬ

Genesis 37:3

አሁንም

ይህ ቃል ታሪኩ ስለ እስራኤልና ዮሴፍ ዳራ መረጃ መቀየሩን የሚያመለክት ነው (ዳራ መረጃ ይመልከቱ)

ስለወደደው

ይህ ወንድማማች ፍቅር ወይም ጓደኛ ፍቅር ወይም ቤተሰብ ፍቅር ያመለክታል ይህ በጓደኛሞችና በቤተሰብ መካከል የሚገለጽ ተፈጥሮአዊ የሰው ልጅ ፍቅር ነው

በስተርጅናው

እስራኤል በአረጀ ጊዜ ዮሴፍን ወልዶአል ማለት ነው:: አት: “እስራኤል በአረጀ ጊዜ የተወለደው” (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)

እርሱ ለእርሱ ……አደረገለት

እስራኤል ለዮሴፍ ..አደረገለት

በኀብረቀለማት ያገጤ እጄ ጠባብ

እጅግ የሚያምር እጄ ጠባብ

በቅን አንደበት ሊያናግሩት አልቻሉም

በሰላም ሊያናግሩት ዘንድ አልቻሉም

Genesis 37:5

ዮሴፍም ሕልምን አለመ ሕልሙንም ለወንድምቹ ሲነግራቸው የባሰ ጠሉት

ይህ በዘፍጥረት 37:6-11 የተቀመጠው ታሪክ ማጠቃለያ ሀሳብ ነው::

የበለጠውኑ ጠሉት

የዮሴፍ ወንድሞች ከዚህ በፊት ከሚጠሉት በላይ ጠሉት

ያየሁትን ይህን ሕልም ልንገራችሁ አድምጡኝ

ሕልሜን ልንገራችሁ አድምጡኝ

Genesis 37:7

አጠቃላይ መረጃ

ስለሕልሙ ዮሴፍ ለወንድሞቹ ይናገራል

እነሆ

“እነሆ” የሚለው ቃል ለሚቀጥለው አስደናቂ ሃሳብ ትኩረት እንዲሰጠው ያነቃል

እኛ ሁላችን

“እኛ” የሚለው ቃል ዮሴፍና ወንድሞቹን ሁሉ ያጠቃልላል (ሁሉን ያቀፈ እኛ ይመልከቱ)

ነዶ እናሥር ነበር

እህል ከታጨደ በኋላ ፍሬው ከገለባው እስኪበጠር ድረስ በየነዶው ታሥሮና ተከምሮ ይጠበቃል

እንሆ

“እነሆ” የሚለው ቃል ዮሴፍ ባየው እንደተደነቀ ይገልጻል

የእኔ ነዶ በድንገት ተነሥታ ቀጥ ብላ ቆመች የእናንተ ነዶዎች ዙሪያዋን ከበው ለእኔ ነዶ ሰገዱላት

እዚህ እንደሰው ነዶዎች ሲቆሙና ሲሰግዱ ይታያል እነዚህ ነዶዎች ዮሴፍንና ወንድምቹን ይወክላሉ (በሰውኛ መንገድ አገላለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)

በላያችን ልትነግሥብን ይሆን? ልትገዛ ይሆን?

እነዚህ ሁለቱም ሀረጐች ተመሣሣይ ትርጉም አላቸው የዮሴፍ ወንድሞች ጥያቄዎችን በመጠቀም ዮሴፍን ማላገድ ጀመሩ እነዚህ በዐረፍተ ነገሮች መልክ ሊገለጹ ይችላሉ አት ንጉሣችን አትሆንም እኛም ለአንተ አንሠግድም (አግናኝ ጥያቄዎችንና ተዛማጅ ተመሣሣይ አባባል ይመልከቱ)

እኛን ልትገዛ

እኛ የሚለው ቃል ዮሴፍን ሳይሆን ወንድሞቹን ያመለክታል (ሁሉን አቀፍና ሁሉን የማያቅፍ “እኛ” ይመልከቱ)

ለሕልሙና ለተናገረው ቃል

ስለ ሕልሙና ልሰተናገረው ቃል

Genesis 37:9

ሌላ ሕልም አለመ

ዮሴፍ ሌላ ሕልም አለመ

አሥራ አንድ ከዋክብት

11 ከዋክብት ቁጥሮች ይመልከቱ

አባቱ ገሠጸው እንዲህም አለው

እስራኤልም ገሠጸው አለውም

ይህ ያየሄው ሕልም ምንድን ነው? እኔና እናትህ ወደ ምድር ተጐንብሰን ልንሰግድል ነው?

እስራኤል ዮሴፍን ለማረም ጥያቄዎችን ይጠቀማል:: ይህ እንደ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል:: አት: “ይህ ያየሄው ሕልም ትክክል አይደለም:: እኔ እናትህና ወንድሞችህ በፊትህ አንሰግድልህም!” (አግናኝ ጥያቄዎችን ይመልከቱ)

ቀኑበት

አንድ ሰው ስኬታማና እጅግ ታዋቂ ከመሆኑ የተነሣ በቁጣ መሞላት ማለት ነው

ነገሩን በልቡ ያዘው

ስለዮሴፍ ሕልም ትርጉም ማሰቡን ቀጠለ ማለት ነው:: አት: “የሕልሙ ትርጉም ምን እንደሆን ማሰቡን ቀጠለ” (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)

Genesis 37:12

ወንድሞችህ በሰኬም በጎችን ይጠብቁ አይደለምን?

እስራኤል በንግግሩ ውስጥ ጥያቄ ይጠቀማል:: ይህ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊገለጽ ይችላል:: አት “ወንድሞችህ በሰኬም በጎችን ይጠብቃሉ” (አግናኝ ጥያቄዎችን ይመልከቱ)

ለመሄድና ወንድሞቹን ለማየት ዮሴፍ እንዲዘጋጅ እስራኤል መጠየቁን የሚገልጽ ነው:: አት “ተዘጋጅ” (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

እነሆኝ

ለመሄድ ተዘጅቸአለሁ(ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

እርሱም እርሱን አለው

እስራኤል ዮሴፍን አለው

ወሬያቸውን አምጣልኝ

ወንድሞቹና በጎቹ እንዴት እንደሆኑ ዮሴፍ ተመልሶ እንዲነግረው እስራኤል ይፈልጋል አት ተመልሰው ያገኘሄውን ንገረኝ ወይም ርፖርት አቅርብልኝ (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)

በሸለቆው

ከሸለቆው

Genesis 37:15

እነሆ ዮሴፍ ሜዳ ላይ ወዲያና ወዲህ ሲባዝን ነበር አንድ ሰውም ዮሴፍን አገኘው

ዮሴፍ ወዲያና ወዲህ ሲባዝን አንድ ሰው ዮሴፍን አገኘው

እነሆ

በትልቁ ታሪክ ስለሌላ ክስተት መጀመሩን የሚያመለክት ነው በቀደሙ ክስተቶች ከነበሩ ሌሎች ሰዎች የሚያሳትፍ ነው በእርስዎ ቋንቋ ይህ የሚገለጽበት መንገድ ሊኖር ይችላል

ምን እያየህ ነው ?

ምን እየፈለግህ ነው?

ወዴት ነው እባክህ ንገረኝ

ወዴት እንደሆነ እባክህ ንገረኝ

ዶታይን

ከሰኬም 22 ኪሎ ሜትር ያህል ርቀት ያለ ቦታ ስም ነው (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)

Genesis 37:18

በሩቅ አዩት

በሩቅ እያለ የዮሴፍ ወንድሞች አዩት

ይገድሉት ዘንድ በእርሱ ላይ ተማከሩ

እርሱን ለመግደል አቀዱ

ያ ሕልም ዐላሚ መጣ

ያ ባለ ሕልም ይሄው መጣ

ስለዚህ አሁንም ኑ

ይህ አባባል ወንድሞቹ ዕቅዳቸውን መተግበር መጀመራቸውን ያሳያል:: አት: (ስለዚህ አሁን ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)

ክፉ አውሬ

አደገኛ አውሬ ወይም ሰው ጨካኝ አውሬ

ቦጫጭቆ በላው

ንጥቆ በላው

ከሕልሞቹም የሚሆነውን እናያለን

ወንድሞቹ ሊገድሉት አቅደዋልና ስለዚህ እስከሞተ ድረስ ሕልሞቹ ይፈጸሙ እንደሆን መናገራቸው አሽሙራዊ/ሽሙጣዊ አባባል ነው:: አት “እስቲ ሕልሞቹ ሲፈጸሙ እናያለን” (በአሽሙር/ሽሙጥ መንገድ የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)

Genesis 37:21

ይህን ሰማ

እነርሱ የመከሩትን ሰማ

ከእጃቸው

ከእጃቸው የሚለው አባባል ሊገድሉት ያቀዱትን የወንድሞቹን እቅድ ያመለክታል:: አት “ከእነርሱ” ወይም “ከእቅዳቸው” (ተዛማጅ ምትክ ቃላት አጠቃቀም ዘይቤ ይመልከቱ)

ሕይወቱን አናጥፋ

ሕይወት ማጥፋት የሚለው ሀረግ አንድን ሰው ስለመግደል በንኀብነት ወይም ለዛ ባለ ቃል በተዘዋዋሪ የሚገልጽ ነው፡፡ አት፡ “ዮሴፍን አንግደለው” (ንኀብነት ወይም ለዛ ባለ ቃል በተዘዋዋራ መንገድ የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)

ደም አታፍስሱ

በግሡ አሉታዊነት ተጨምሮበታል ደግሞም ደምን ማፍሰስ አንድን ሰው ስለመግደል በንኀብነት ወይም ለዛ ባለ ቃል በተዘዋዋሪ የሚገልጽ ነው፡፡ አት የማንኛውንም ሰው ደም አታፍስሱ ወይም አትግደሉት (በአሉታዊነት አዎንታዊነትን የመግለጽ ዘይቤና ንኀብነት ወይም ለዛ ባለ ቃል በተዘዋዋራ መንገድ የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)

እጃችሁን አታንሡበት

አታቆስሉት ወይም አትጉዱት ማለት ነው አት አትጉዱት (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)

ከእጃቸው ሊያተርፈው

ይህ እንደ አዲስ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል:: “ሮቤል ይህ ያለው ዮሴፍን ሊታርፈው ዘንድ ነው”

ከእጃቸው

ከእጃቸው የሚለው አባባል ሊገድሉት ያቀዱትን የወንድሞቹን እቅድ ያመለክታል:: አት “ከእነርሱ” ወይም “ከእቅዳቸው” (ተዛማጅ ምትክ ቃላት አጠቃቀም ዘይቤ ይመልከቱ)

ሊመልሰው

እናም ሊመልሰው

Genesis 37:23

እንደ ደረሰ

ይህ ሐረግ በታሪኩ ተፈላጊ ክስተት ለመጠቆም ተጠቅሞአል በቋንቋህ እንዲህ ዓይነት ካለ በዚህ ቦታ ሊጠቀሙ ይችላሉ

በኀብረ ቀለማት ያገጠች እጀ ጠባቡን ገፈፉት

በኀብረ ቀለማት ያገጠች እጀ ጠባቡን ከላዩ ላይ ቀደዱት

ያገጠች ልብስ

ያገጠች እጀ ጠባብ፤ በዘፍጥረት 37:3 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ

Genesis 37:25

እንጀራም ሊበሉ ተቀመጡ

እንጀራ በአጠቃላይ መግብን ያመለክታል አት ምግባቸውን ለመብላት ተቀመጡ ወይም የያዕቆብ ወንድሞች ምግባቸውን ሊበሉ ተቀመጡ (ክፍልን እንደ ሙሉና ሙሉን እንደ ክፍል የመግልጽ ዘይቤ ይመልከቱ)

ዐይኖቻቸውንም አንስተው አዩ እነሆም… የግመል ጓዝ

እዚህ አንስተው አዩ አንድሰው በውኑ አይኑን እንሰቶ እንደሚያይ ተደርጐ ተነግሮአል ደግሞም እነሆ የሚለው ቃል ሰዎች ላዩት ትኩረት ለመስጠት ተጠቅሞአል:: አት: “አይኖቻቸውን አነሡ እናም ወዲያውም የግመል ጓዝ አዩ” (ዘይቤያዊ አባባል ይመልከቱ)

ተሸክመው

ጭነው

ኬርቤ

ቅመማቅመም

በለሳን

የቆዳ ቁስለትን የሚፈውስና የሚከለክል ጣፋጭ ጣዕም ያለው ቅባታማ ነገር “መድኃኒት”

ጭነው ወደ ግብጽ የሚወርዱ

ወደ ግብጽ የሚያመጡ ይህ ግለጽ ሊደረግ ይችላል አት ለመሸጥ ወደ ግብጽ የሚወርዱ ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ

ወንድማችንን መግደልና ደሙን መሸሸግ ምን ይጠቅማናል?

ይህ እንደዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል:: አት “ወንድማችንን በመግደልና አሟሟቱን በመደበቅ እንጠቀምም” (አግናኝ ጥያቄዎችን ይመልከቱ)

ደሙን መሸሸግ

የዮሴፍን ሞት በደበቅን የሚገልጽ ምሳሌዊ አነጋገር ነው:: አት “አሟሟቱን መደበቅ” (ዘይቤያዊ አባባል ይመልከቱ)

Genesis 37:27

ለእስማኤላዊያን

የእስማኤል ዘር ለሆኑ ለእነዚህ ሰዎች

እጃችንን በእርሱ ላይ አናንሳ

ይህም “አናቆስለው” ወይም “አንጉዳው” ማለት ነው አት: “አንጉዳው” (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)

ወንድማችን ሥጋችን ነው

ሥጋ የሚለው ዘመድ ለሚለው ቃለ የሚቆም ምትክ ቃል ነው:: አት: “እርሱ የሥጋ ዘመዳችን ነው” (ተዛማጅ ምትክ ቃላትን የመጠቀም ዘይቤ ይመልከቱ)

ወንድሞቹም የእርሱን ነገር ሰሙት

የይሁዳ ወንድሞች ሰሙት ወይም የይሁዳ ወንድሞች በሐሳቡ ተስማሙ

ምድያማዊያን ….. እስማኤላዊያን

ሁለቱም ስሞች የዮሴፍ ወንድሞች ያገኙአቸው ተመሣሣይ ነጋዴዎችን ያመለክታል

ለሃያ ጥሬ ብር

ለሃያ ጥሬ ብር ዋጋ (ቁጥሮችን ይመልከቱ)

ዮሴፍን ወደ ግብጽ የዘውት ሄዱ

ዮሴፍን ወደ ግብጽ ወሰዱት

Genesis 37:29

ሮቤል ወደ ጉድጓዱ ተመልሶ ሲያይ ዮሴፍን በማጣቱ

ሮቤል ወደ ጉድጓዱ ተመልሶ ዮሴፍን በማጣቱ እነሆ ተገረመ:: “እነሆ” የሚለው ቃል ሮቤል ዮሴፍ በሄዱን ባወቀ ጊዜ መገረሙን ያሳያል::

ልብሱን ቀደደ

ይህ የጥልቅ ጭንቀትና ሀዘን ምልክት ነው:: ይህ በግልጽ ሊገለጽ ይችላል:: አት: እጅግም ስላዘነ ልብሱን ቀደደ (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

ብላቴናው የለም እንግዲህ እኔ ወዴት እሄዳለሁ?

የዮሴፍ መጥፋቱን ችግር ትኩረት ለመስጠት ሮቤል ጥያቄ ይጠቀማል:: አት: “ብላቴናው ሄዶአል እንግዲህ ወደ ቤት መመለስ አልችልም” (አግናኝ ጥያቄዎችን ይመልከቱ)

Genesis 37:31

የዮሴፍ እጀ ጠባብ

አባቱ ያዘጋጀለት ያጌጠችውን እጀ ጠባብ ያመለክታል

ደም

የፍዬል ደም

አምጥተው

እጀ በባቡን አምጥተው

ቦጫጭቆ በልቶታል

በልቶታል

በእርግጥም ዮሴፍ ተቦጫጭቆአል

ያዕቆብ የዮሴፍን አካል ክፉ አውሬ እንደገነጣጠለ አሰበ:: አት: “በእርግጥም ዮሴፍን ቦጫጭቆታል” (ተሻጋሪና የማይሻገር ግሥ ይመልከቱ)

Genesis 37:34

ያዕቆብ ልብሱን ቀደደ

ይህ ጥልቅ መጨነቅንና ሀዘንን የሚያመለክት ነው ይህ በግልጽ ሊገለጽ ይችላል አት ያዕቆብ እጅግ ስላዘነ ልብሱን ቀደደ (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

በወገቡም ማቅ ታጥቆ

ወገብ የሰውነት መሀከለኛው አካል ነው አት ማቅ ለብሶ (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

ተነሡ

እዚህ አባታቸውን ለማጽናናት የልጆች መጥጣት እንደ መነሣት ተደርጐ ተገልጾአል:: አት: “ወደ እርሱ መጡ” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)

እርሱ ግን ሊጽናና ባለመቻሉ

ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል:: አት: “ነገር ግን እንዲያጽናኑት አልፈቀደም” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)

ወደ ሙታን ሥፍራ እያዘንሁ እወርዳለሁ

ከዛሬ ጀምሮ እስከሚሞት ድረስ እንደሚያዝን ይገልጻል:: አት: “በሚሞትበትና ወደ ሙትን ሥፍራ በሚወርድበትም ጊዜም በእርግጥ እያዘንኩ ይሆናል” (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

ምድያማዊያን ሸጡት

ምድያማዊያን ዮሴፍን ሸጡት

ለዘበኞች አለቃ

ንጉሡን ለሚጠብቁ ዘበኞች መሪ