Genesis 32

Genesis 32:1

መሃናይም

ተርጓሚዎች በግርጌ ማስታወሻዎች ሊጨምሩ ይችላሉ:: መሃናይም የሚለው ስም “ሁለት ሰፈሮች” ማለት ነው

Genesis 32:3

ሴይር

ይህ በኤዶምያስ ግዛት ተራራማው ቦታ ነው:: ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ::

ጌታዬን ዔሣውን እንዲህ ትሉታላችሁ “አገልጋይህ ያዕቆብ እንዲህ ብሎአል በሉት “እስካሁን …. በፊትህ’”

ይህ በጥቅስ ውስጥ የሚገኝ ጥቅስ አለው:: ቀጥታው ጥቅስ እንደ ተዘዋዋሪ ጥቅስ ሊገለጽ ይችላል:: አት: “ ‘ይህ ለጌታዬ ለዔሣው ሊነግር የሚወደው ነው:: እስከዚህ እንዳለሁት ……በፊቱ’” (ጥቅስን በጥቅስ ውቅጥና ቀጥታና ተዘዋዋሪ ጥቅሶችን ይመልከቱ)

ጌታዬ ዔሣው

ያዕቆብ ወንድሙን ጌታው አድርጐ በማቅረብ የትህትና ቃል ይጠቀማል

አገልጋይህ ያዕቆብ

ያዕቆብ ራሱን እንደአገልጋዩ በማድረግ የትህትና ቃል ይጠቀማል

በአንተ ፊት ሞገስ ባገኝ

ሞገስ ማግኘት የሚለው ሀረግ በሌሎች ሰዎች ዘንድ ተቀባይነትን ማትረፍን የሚገልጽ ፈሊጣዊ አባባል ነው አት “መቀበልህን እንዲታረጋግጥልኝ” (ፈሊጣዊ አነጋገር ተመሣሣይ ምትክ ቃላትና ዘይቤያዊ አባባሎች ይመልከቱ)

Genesis 32:6

አራት መቶ ሰዎች

4ዐዐ ሰዎች ቁጥሮች ይመልከቱ

ፍርሃት

አንድ ሰው በራሱ ወይም ከሌሎች ሥጋት የሚፈጥር ጉዳት ሲደረስበት የማሰማው ስሜት ነው

ጭንቀት

ተስፋ መቁረጥ ወይም መረበሽ

በአንደኛው ሠፈር ላይ አደጋ ቢጥል ሌላው ሠፈር ሊያመልጥ ይችላል

እዚህ ሠፈር ሰዎችን ይወክላል አት በአንዱ ሠፈር ባለው ሰው አደጋ ቢጣል በሌላው ሠፈር ያለው ሰው ያመልጣል፡፡ (ተመሣሣይ ምትክ ቃላት የመጠቀም ዘይቤ ይመልከቱ)

Genesis 32:9

የአባቴ የአብርሃም አምላክ የአባቴ የይስሐቅ አምላክ ሆይ

ይህ ለተላያዩ አማልክት ሳይሆን ሁሉም ያመለኩትን አንድ እግዚአብሔርን ያመለክታል አት የአያተ የአብርሃምና የአባተ የይስሐቅ አምላክ እግዚአብሔር (ግምታዊ እውቀትና ጥብቅ መረጃ ይመልከቱ)

ወደ አገርህና ወደ ዘመዶችህ ተመለስ እኔም በጐ ነገርን አደርግልሃለሁ ያልከኝ እግዚአብሔር ሆይ

ይህ በጥቅ ውስጥ የሚገኝ ጥቅሰ ነው:: በተዘዋዋሪ ጥቅስ መልክ ሊገለጽ ይችላል:: አት: “ወደ አገረና ወደ ሕዝቤ እንድመለስና በጐ ነገርንም አደርግልሃለሁ ያልከው እግዚአብሔር”

ወደ ዘመዶችህ

ወደ ቤተሰብህ

በጐ ነገር አደርግልሃለሁ

መልካም ነገር አደርግልሃለሁ ወይም በመልካምነት እንከባከብሃለሁ

እኔ ባሪያህ እስካሁን ላደረክልኝ የቃልኪዳን ቸርነትና ታማኝነት ብቁ አይደለሁም

ረቂቅ ስሞች ቸርነትና ታማኝነት እንደ ቸር እና ታዛዥ ሊገለጹ ይችላሉ አት እኔ ባሪያህ እስካሁን ላደረክልኝ የቃልኪዳን ታማኝ አይደለሁም ወይም ታዛዥ አይደለሁም (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተነገር ይመልከቱ)

ባሪያህ

“እኔ” የሚለው በትህትና ቃል ሲገለጽ ነው

አሁን ግን የሁለት ክፍል ሠራዊት ሆንሁ

ሆንሁ የሚለው ሐረግ ያለውን ሀብት የሚገልጽ ፈሊጣዊ አባባል ነው:: አት: “አሁን ግን ከእኔ ጋር በሁለት ክፍል ሠራዊት በቂ ሰዎች መንጋዎችና ሀብት አሉኝ” ፈሊጣዊ አባባል ይመልከቱ

Genesis 32:11

አድነኝ

አትርፈኝ

ከወንድሜ እጅ ከዔሣው እጅ

እዚህ “እጅ” ጉልበትን ያመለክታል ሁለቱም ሀረጐች ተመሣሣይ ትርጉም አላቸው ሁለተኛው የሚገልጸው ያዕቆብ የሚያስበው ወንድመ ዔሣው እንደሆነ ነው፡፡ አት፡ ከወንድሜ ከዔሣው ጉልበት ወይም ከወንድሜ ከዔሣው (ተመሣሣይ ምትክ ቃል ወይም ተጓዳኝ ንጽጽር ይመልከቱ)

እንዳያጠፋ እኔ እፈራለሁና

እንደሚያጠፋ ፈርቼያለሁና

ነገር ግን አንተ ራስህ አበለጽግሃለሁ ዘርህን ሊቈጠር….

ይህ በጥቅስ ውስጥ ያለ ጥቅስ ነው እንደተዘዋዋሪ ጥቅስ ሊገለጽ ይችላል:: አት: “ነገር ግን አንተ ራስህ አብለጽግሃለሁ እናም የዘረንም ቁጥር..” (ጥቅሶችን በጥቅስ ውስጥና ቀጥተኛና በዘዋዋሪ ጥቅችን ይመልከቱ)

አበለጽግሃለሁ

መልካም ነገርን አደርግልሃለሁ ወይም በመልካምነቴ አሳይሃለሁ

ዘርህን እንደ ባህር አሸዋ አበዛዋለሁ

የያዕቆብን ዘር ቁጥር እጅግ ብዙ ማድረጉ ቁጥሩ እንደ ባህር አሸዋ ቁጥር እንደሚሆን ተደርጐ ተነግሮአል (ተመሣሣይ ቃላት የመጠቀም ዘይቤ ይመልከቱ)

ሊቆጠር እንደማይችል

ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል አት: “ያም ከቁጥራቸው የተነሣ ማንም መቁጠር እስከማይችል” (ተሻጋሪ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)

Genesis 32:13

ሁለት መቶ

2ዐዐ (ቁጥሮችን ይመልከቱ)

ሃያ …. ሠላሣ …. አርባ … አሥር

20 …. 30 …. 40 ….10 (ቁጥሮች ይመልከቱ)

ግልገሎች

እየጠቡ ያሉ ለጋ እንስሳት

እነዚህንም መንጐች በየወገኑ ከፍሎ በባሪያዎች እጅ አደረጋቸው

እዚህ “በእነሱ እጅ” በእነሱ ቁጥጥር ሥር አደረገ ማለት ነው:: አት በየወገኑ ከፈላቸው እናም እያንዳንዱን መንጋ በእያንዳንዱ ባሪያ ቁጥጥር ሥር አደረገ (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)

መንጋውንና መንጋውን አራርቁት

አንዱ መንጋ ከሌላው መንጋ በርቀት እንዲጓዝ አድረጉ

Genesis 32:17

መመሪያ ሰጠው

አዘዘው

በፊትህ ያለው… የማን ነው? ብሎ የጠየቀህ እነደሆነ

ይህ በጥቅስ ውስጥ ያለ ጥቅስ ነው እንደ ተዘዋዋሪ ጥቅስ ሊገለጽ ይችላል:: አት: “የማን ነህ? ወዴትስ ተሄዳለህ? የምትነዳውስ ይህ ሁሉ ከብት የማን ነው? ብሎ ቢጠይቅህ” (ጥቅስ በጥቅስ ውስጥ እና ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ ጥቅሶች ይመልከቱ)

የማን ነህ?

ጌታህ ማን ነው?

በፊትህ ያለው ይህ ሁሉ ከብት የማን ነው?

በፊትህ ያለው የዚህ ሁለ ከብት ባለቤት ማን ነው?

በዚያን ጊዜ አንተ ለጌታዬ ለዔሣው እጅ መንሻ የሰደደው የባሪያህ የያዕቆብ ነው እርሱም ደግሞ ከኋላችን እየመጣ ነው፤ በለው

ይህ በጥቅስ ውስጥ የሚገኝ ጥቅስ ነው በተዘዋዋሪ ጥቅስ መልክ ሊገለጽ ይችላል፤ አት፤ “በዚያን ጊዜ እነዚህ ሁሉ የአገልጋይህ የያዕቆብ ናቸው፤ ለጌታዬ ለዔሣው እጅ መንሻ የሰደዳቸው ናቸው፤ እርሱም ሊገናኝህ ከበስተኋላችን እየመጣ ነው፤ ብለህ እንዲትነግረው እፈልጋለሁ::” (ጥቅስ በጥቅስ ውስጥ እና ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ ጥቅሶች ይመልከቱ)

የአገልጋይህ የያዕቆብ ናቸው

የዕቆብ ራሱን ትህትናን በተሞላ መንገድ የዔሣው ባሪያ አድርጐ ያቀርባል

ለጌታዬ ለዔሣው

ያዕቆብ በትህትና ዔሣውን እንደ ጌታው መቁጠሩን ያመለክታል

ከእኛ ኋላችን እየመጣ ነው

እኛ የሚናገረውን ባሪያ ያመለክታል እናም ሌሎች ባሪያዎችም ለዔሣው እጅ መንሻ ይዘው እየመጡ እንዳለ ይገለጻል (ብዙና ነጠላ “እኛ” ይመልከቱ)

Genesis 32:19

ለሁለተኛው ቡድን መመሪያ ሰጠ

ሁለተኛውን ቡድን አዘዘ

ይህኑን ትነግሩታላችሁ ባሪያህ ያዕቆብ

አማራጭ ተገቢ ትርጉሞች 1) “ደግሞም እንዲህ ትነግሩታላችሁ ባሪያህ ያዕቆብ” 2) “ደግሞም እንዲህ ትላላችሁ ባሪያህ ያዕቆብ”

አስደስት ይሆናል

አረጋጋው ይሆናል ወይም ቁጣው እንዲርቅ አደርግ ይሆናል

ይቀበለኛል

በርኀራኄ ይቀበለኛል

የያዕቆብ እጅ መንሻ ከእርሱ አስቀድሞ ተላከ

እዚህ እጅ መንሻ እጅ መንሻውን ይዘው የሄዱ ባሪያዎች ይወክላል (ምትክ አባባሎችን የመጠቀም ዘይቤ ይመልከቱ)

እርሱ ራሱ ግን እዚያው አደረ

እዚህ “ራሱ” ያዕቆብ ከባሪያዎቹ ጋር እንዳለሄደ አበክሮ ይናገራል (ተጣቃሽ ተውላጤ ስም ይመልከቱ)

Genesis 32:22

ሁለት ሴት ባሪያዎቹ/አገልጋዮቹ

ሁለት ባሪያ/አገልጋይ ሚስቶቹ፤ ዘለፋና ባላ ማለት ነው

የወንዝ መልካ

በወንዝ ጥልቅ ያልሆነ በቀላሉ የሚያሻግር ቦታ

ያቦቅ

ይህ የወንዝ ስም ነው ስሞችን እንዴት እንደሚተረጉሙ ይመልከቱ

ንብረቱን ሁሉ

ያለውን ነገር ሁሉ

Genesis 32:24

እስኪነጋ

ንጋት ድረስ

የጭኑ ሹልዳ ሲታገለው ደነዘዘ

ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ልገለጽ ይችላል፤ አት: “በሚታገልበት ጊዜ የሚታገለው ሰው የያዕቆብን ሹልዳ ጐዳው” (ተሻጋሪ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)

ጭን

ከዳሌ ጋር የተያያዘ ላይኛው የእግር አካል ነው

ሊነጋ ሲል

ጸሐይ ከመውጣትዋ በፊት

መባረክ

በአንድ ሰው ላይ በረከትን ማዘዝና ለዚያ ሰው መልካም ነገር እንዲሆኑለት ማድረግ ነው

ካልባረክሄኝ አልለቅህም

ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ልገለጽ ይችላል፤ አት: “በእርግጥ አልለቅህም መጀመሪያ ባርከኝና ከዚያም እለቅሃለሁ” (ተሻጋሪ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ) (ድርብ አሉታዊ አባባሎች ይመልከቱ)

Genesis 32:27

እስራኤል

ተርጓሚዎች የግርጌ መስታወሻ እንደሚከተለው ሊጨምሩ ይችላሉ እስራኤል የሚለው ስም ከእግዚአብሔር ጋር ይታገላል ማለት ነው ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ

ሰዎች

ሰዎችን በገሃድ የሚገልጽ ነው

Genesis 32:29

እርሱም ስሜን ለምን ትጠይቃለህ? አለው

እርሱም ስለ ስሜ ለምን ተቀጠይቃለህ አለው ይህ አግናኝ ጥያቄ ያዕቆብን የሚያደነግጠው የሚገሥጸውና በእርሱና ከእርሱ ጋር ሲታገል በቆየው ሰው መካከል ምን እንደተከሰተ እንዲያስብ የሚያደርገው ነው:: አት: “ስሜን አትጠይቅ” (አግናኝ ጥያቄዎችን ይመልከቱ)

ጵንኤል

ተርጓሚዎች የግርጌ መስታወሻ እንደሚከተለው ሊጨምሩ ይችላሉ:: “ጵንኤል” የሚለው ስም “የእግዚአብሔር ፊት” ማለት ነው:: (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)፡፡

ፊት ለፊት

“ፊት ለፊት” ሁለት ሰዎች በቅርበት በአካል የሚተያዩበት ማለት ነው::

ሕይወቴ ተርፋለች

ይህ በሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል አት ሕይወቴን አትርፎአታል:: (ተሻጋሪ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)

Genesis 32:31

ከዚህም የተነሣ እስከ ዛሬ ድረስ

ይህ ታሪኩ ወደ እስራኤል ዘር ዳራ ትረካ እንተለወጠ አመላካች ነው (የዳራ መረጃ ይመልከቱ)

የጭኑ ሹልዳ

ሹልዳን ከጭኑ ጋር የሚያገናኝ የጡንቻ ሥጋ ያመለክታል

ተነክቶ ነበር

ሲታገል ተነክቶ ነበር