Genesis 29

Genesis 29:1

የምሥራቅ ሰዎች

ከከነዓን ምድር በስተምሥራቅ የሚገኙ የጳዳን አራም ሰዎች ማለት ነው::

እነሆ በአንድ ሜዳ ላይ ሶስት የበግ መንጋዎች ተኝተው በነበሩበት

እነሆ የሚለው ቃል በትልቁ ታሪክ ውስጥ አንድ ሌላ ክስተት መጀመሩን ያመለክታል:: በሚትተረጉሙበት ቋንቋ ይህን የመግለጽ መንገድ ሊኖሮት ይችላል::

ከዚያ ጉድጓድ

ከዚሁ ጉድጓድ ይህ ሀረግ ታሪኩን ወደ ዳራው መረጃ ይመልስና እንዴት እረኞች በጐችን ውሃ እንደሚያጠጡ ይናገራል

እነርሱ ውሃ ያጠጣሉ

“እረኞች ውሃ ያጠጣሉ” ወይም “በጐችን የሚጠብቁ ውሃ ያጠጣሉ”

የጉድጓዱ አፍ

አፍ ጉድጓዱ የተከፈተበትን ቦታ ያሳያል:: አት: “ጉድጓዱ የተከፈተበት ቦታ”

Genesis 29:4

ያዕቆብም እነርሱን አለ

ያዕቆብም እረኞቹን አለ

ወንድምቼ

ይህ ለእንግዶች በትህትና ሰላምታ የማቅረብ መንገድ ነው

የናኮር ወንድ ልጅ ላባ

አዚህ ወንድ ልጅ ወንድ ዘርን ያመለክታል ሌላ ተገቢ ትርጉም የናኮር የልጅ ልጅ ላባ

እነሆ ተመልከት ራሔል በጎችን እየነዳች በመምጣት ላይ ነች

አሁን ተመልከት የእርሱ ሴት ልጅ ራሔል ከበጎች ጋር በመምጣት ላይ ነች

Genesis 29:7

ገና ቀትር ነው

“ገና ጸሐይ በሰማይ ላይ ነች/ጊዜው ገና ነው” ወይም “ጸሐይ ገና በማብራት ላይ ነች”

መንጎች እስኪሰበሰቡ

ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት: “መንጐችን እስኪሰበስቡ” (ተሻጋረ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተነገር ይመልከቱ)

መሰብሰብ

ይህም ሌሊቱን እንዲያሳልፉ በቅጥር ውስጥ መሰብሰብ ማለት ነው:: የዚህ ሙሉ ትርጉም ግልጽ ሊደረግ ይችላል:: (ግምታዊ እውቀት እና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

ወደ ግጦሽ ይመለሱ

በሜዳ ያለውን ሣር ይመገቡ

ውሃ ሊናጠጣቸው አንችልም

ውሃ ሊናጠጣቸው መጠበቅ አለብን ይህ ፈቃደኝነት ሳይሆን ጊዜን በሚመለከት ነው

መንጐቹ ሁሉ እስኪሰበሰቡ

ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት: “ሌሎች እረኞች መንጐቻቸውን እስኪሰበስቡ” (ተሻጋረ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተነገር ይመልከቱ)

ከጉድጓዱ አፍ

እዚህ አፍ ጉድጓዱ የተከፈተውን ቀዳዳ ያመለክታል አት ከጉድጓዱ ወይም ጉድጓዱ በተከፈተበት (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)

Genesis 29:9

የእናቱ ወንድም

አጐቱ

የጉድጓዱ አፍ

እዚህ “አፍ” የተከፈተበትን ቦታ ያመለክታል:: አት: “ጉድጓዱ” ወይም “ጉድጓዱ የተከፈተበትን ቦታ” (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)

Genesis 29:11

ያዕቆብም ራሔልን ሳማት

በጥንታዊቷ ቅርብ ምሥራቅ በመሳም ሰላምታ መለዋወጥ የተለመደ ነው:: ነገር ግን በወንዶች ዘንድ እምብዛም የታወቀ ነው:: በሚትተረጉሙበት ቋንቋ ባህል እንዲህ ዓይነቱ ስሜትን በመግለጽ ዘመዳሞች ሰላምታ የመለዋዋጥ ነገር ካለ ይህን ይጠቀሙ:: ከሌለ ግን ሌላ ተገቢ አባባል ይጠቀሙ::

ድምጹን ከፍ አድርጐ አለቀሰ

ያዕቆብ የሚያለቅሰው ደስተኛ በመሆኑ ነው የዚህ ዐረፍተ ነገር ሙሉ ትርጉሙ ግልጽ ሊደረግ ይችላል:: (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

የአባትዋ ዘመድ

ለአባትዋ የሚዛመድ

Genesis 29:13

የእርሱ እኀት ልጅ

የእኀቱ ልጅ

አቀፈው

አቀፈው

ሳመው

በጥንታዊቷ ቅርብ ምሥራቅ በመሳም ለዘመድ ሰላምታ ማቅረብ የተለመደ ነው:: ነገር ግን ይህ በወንዶች መካከል የታወቀ ነው:: በሚተረጉሙት ቋንቋ ለዘመድ የሚቀርብ ሰላምታ ስሜትን የሚገልጽ ከሆነ ይህን ይጠቀሙበት:: ካለሆነ ግን ሌላ ተገቢ አባባል ይጠቀሙ::

ያዕቆብም ሁኔታውን ሁሉ ለላባ ነገረው

“ከዚያም ያዕቆብ ለራሔል የነገረውን ሁሉ ለላባ ነገረው”

የአጥንቴ ፍላጭ የሥጋዬ ቁራጭ

እነዚህ ሀረጐች በቀጥታ የሚዛመዱ ናቸው:: አት: “የእኔ ዘመድ” ወይም “የቤተሰቤ አባል” (ተዛማጅ ምትክ ቃላት የመጠቀም ዘይቤ ይመልከቱ)

Genesis 29:15

ዘመዴ በመሆንህ ብቻ በነጻ ሊታገለግለኝ አይገባምና…?

ስለሚሠራለት ሥራ ለያዕቆብ መክፈል ስለአለበት ላባን ይህንን አግንኖ ለመናገር ጥያቄ ይጠቀማል:: ይህ በአዎንታዊ መንገድ ሊገለጽ ይችላል:: አት: “ዘመዴ ቢትሆንም ለሚትሠራልኝ መክፈል በእርግጥ ትክክል ነው” See:RhetoricalQuestionandLitotes

የልያ ዐይን ልም ነው

ተገቢ ትርጉሞች 1 የልያ ዓይኖች ልም ነበሩ 2 የልያ ዐይኖች ታማሚ ነበሩ

ያዕቆብ ራሔልን ወደደ

እዚህ ወደደ የሚለው ቃል በአንድ ወንድና ሴት መካከል የሚሆን ስሜታዊ ወዋደድን ያመለክታል

Genesis 29:19

ለሌላ ወንድ ከሚሰጣት ይልቅ

ለሌላ ወንድ ከሚድራት ይልቅ

እነዚያ ጥቂት ቀናት ብቻ ሆኖ ታየው

“ነገር ግን ጊዜው ጥቂት ቀናት ሆኖ ታየው”

ለእርስዋ ካለው ፍቅር

“ለእርስዋ ያለውን ፍቅር ስመዝን” ወይም “ለእርስዋ ካለው ፍቅር የተነሣ”

Genesis 29:21

እንዳገባት ዘንድ ሚስቴን ስጠኝ ቀኔ ተፈጽሞአልና

ቀኔ ተፈጽሞአል የሚለው ሀረግ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: ይህ emphatic ዐረፍተ ነገር ነው:: አት: “ለአንተ መሥራት የሚገባኝን ጊዜ ስለፈጸምሁ እንዳገባት ሚስቴን ስጠኝ” ወይም “ለሰባት ዓመታት ስላገለገልሁ እንዳገባት ራሔልን ስጠኝ” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)

ሠርግ አዘጋጀ

የጋብቻ ሠርግ አዘጋጀ ምናልባት ላባን ሌሎች ሰዎች እንዲያዘጋጁ አደረገ:: አት: “ሌሎች የጋብቻ ሠርግ እንዲያዘጋጁ አደረገ”:: (ተዛማጅ ምትክ ቃላት አጠቃቀም ዘይቤ ይመልከቱ)::

Genesis 29:23

አብሮአት ተኛ

ይህ የሚገልጸው ምሽት ስለነበረና ስላላያት ከልያ ጋር መሆኑን ያዕቆብ አላወቀም ነበር:: የዐረፍተ ነገሩ ሙሉ ትርጉም ግልጽ ሊደረግ ይችላል:: (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

ላባን ዘለፋ የተባለች አገልጋዩን ለልጁ ለልያ ደንገጡር እንድትሆን ሰጣት

እዚህ ጸሐፊው ላባን ዘለፋን ለልያ እንደሰጠ መረጃ ይሰጣል፡፡ ዘለፋን ለልያ ከሠርግ በፊት ሳይሰጣት አይቀርም:: (ታሪካዊ ዳራ መረጃ ይመልከቱ)

እነሆ ልያ ሆና ተገኘች

ያዕቆብም ልያ በአልጋ አብሮአት በማየቱ ተገረመ:: “እነሆ” የሚለው ቃል ያዕቆብ ባየው ነገር እንዴት እንደተደነቀ የሚያሳይ ነው፡፡

ምነው እንደዚህ አደረግህብኝ?

ያዕቆብ ቁጣውንና መገረሙን ለመግለጽ ጥያቄ ይጠቀማል ይህ ቅኔ አዘልጥያቄ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡ “ይህን ለእኔ ታደርጋለና ብዬ አላምንህም” (See: RhetoricalQuestion)

ያገለገልሁህ ለራሔል ብዬ አልነበረምን?

ያዕቆብ እነዚህን ጥያቄዎች የሚጠቀመው ላባን ያታለለውን ጉዳቱን ለመግለጽ ነው ይህ ቅኔ አዘል ጥያቄ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊገለጽ ይችላል ራሔልን ለማግባት ሰባት ዓመት አገልግየሃለሁ (See: Rhetorical Question)

Genesis 29:26

እንሰጥ ዘንድ ወግ አይደለም

በቤተሰባችን አንሰጥም

ለዚህች ሴት ልጅ ይህን የጫጉላ ሳምንት ፈጽም

የልያን ጫጉላ ሳምንት ፈጽም

ሌላኛይቱን ደግሞ እንሰጣለን

የዚህ ሙሉ ትርጉም ግልጽ ሊደረግ ይችላል አት በሚቀጥለው ሳምንት ደግሞ ራሔልን እንሰጥሃለን (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

Genesis 29:28

ያዕቆብም እንዲሁ አደረገ እናም የልያን ሳምንት ፈጸመ

ያዕቆብ ላባን የጠየቀውን አደረገ እናም የልያን ጫጉላ ሳምንት ማክበርን ፈጸመ

ባላ

ይህ የራሔል ሴት አገልጋይ ስም ነው:: (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)

ያዕቆብም ከራሔል ጋር ተኛ

ጋብቻዊ ግንኙነት እንደፈጸሙ የሚገልጽ አክብሮታዊ ወይም ለዛ አባባል ነው

ራሔልን ወደዳት

በአንድ ወንድና በአንድ ሴት መካከል የሚሆን ስሜታዊ ፍቅር ያመለክታል

Genesis 29:31

ልያ አልተወደደችም

ይህ ተሻሪ ግሥ በያዘ መልክ ወይም በገቢር ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል:: አት: “ያዕቆብ ልያን አልወደዳትም” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)

እንዳልተወደደች

ያዕቆብ ራሔልን ከልያ ይልቅ እንደወደዳት በማተኮር አግንኖ የሚናገር ነው አት ከራሔል አሳንሶ ወደዳት (አግንኖና በገሃድ የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)

ማሕጸንዋን ከፈተላት

እግዚአብሔር ልያ እንዲትጸንስ ማድረጉ እግዚአብሔር ማሕጸንዋን እንደከፈተ ተደርጐ ተነግሮአል:: (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)

መካን ነበረች

ሊትጸንስ አልቻለችም

ልያ ጸነሰች ልጅም ወለደች

ልያ ጸነሰች ወንድ ልጅም ወለደች

ስሙን ሮበል አለችው

ተረጓሚዎች የሚከተለውን አንደ ግርጌ ማስታወሻ ተጨማሪ አድርገው ሊያቀርቡ ይችላሉ:: ሮበል የሚለው ስም ‘ወንድ ልጅ አየሁ’ ማለት ነው (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)

እግዚአብሔር መከራዬን ስለተመለከተልኝ

ልያ ያዕቆብ ስላልተቀበላት በስሜታዊ ሕመም ነበራት:: “መከራ” የሚለው ረቂቅ ስም እንደ ግሥ ሊገለጽ ይችላል:: አት: “እግዚአብሔር እንደተሰቃየሁ አየኝ” (ረቂቅ ስሞች ይመልከቱ)

Genesis 29:33

እንደገናም ጸነሰች

እንደገናም ልያ ጸነሰች

ልጅ ወለደች

ወንድ ልጅ ወለደች

ስሙን ስምዖን ብላ ጠራችው

ተረጓሚዎች የሚከተለውን አንደ ግርጌ ማስታወሻ ተጨማሪ አድርገው ሊያቀርቡ ይችላሉ:: “ስምዖን የሚለው ስም ‘ተሰማ’ ማለት ነው (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)

ባሌ ያቀርበኛል

ባሌ ያቅፈኛል

ሶስት ወንዶች ልጆች ስለወለድሁለት

ለእርሱ ሶስት ወንጆ ልጆች ወለድሁለት

ስው ሌዊ ይባላል

ተረጓሚዎች የሚከተለውን አንደ ግርጌ ማስታወሻ ተጨማሪ አድርገው ሊያቀርቡ ይችላሉ:: “ሌዊ የሚለው ስም ‘የተጠጋ’ ማለት ነው (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)

Genesis 29:35

እንደገናም ጸነሰች

ልያ እንደገና አረገዘች

ወንድ ልጅ ወለደች

ወንድ ልጅን ወለደች

ስሙንም ይሁዳ ብላ ጠራችው

ተረጓሚዎች የሚከተለውን አንደ ግርጌ ማስታወሻ ተጨማሪ አድርገው ሊያቀርቡ ይችላሉ:: “ይሁዳ የሚለው ስም ‘ምሥጋና’ ማለት ነው (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)