Genesis 27

Genesis 27:1

ዓይኖቹ ደክመው

ይህ የሚናገረው ዓይኖች እንደ መብራት ብርሃን እየቀነሱ እንደሄዱ እና ማየት ወደ መሳን ደረጃ እንደደረሱ ነው:: አት: “ዓይኖቹ ማየት ተስኖአቸው” ወይም “ዓይኖቹ ወደ መታወር ደርሰው” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)::

እርሱም እርሱን አለው

“ዔሣው መለሰለት”“ዔሣው መለሰለት”

እነሆ አለው

“እነሆ አለሁ” ወይም “እየሰማሁ ነኝ” በዘፍጥረት 22:1 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ::

እርሱም አለው

“ከዚያም ይሥሐቅም አለ”

ይሄው ተመልከት

“ይኼው ተመልከት” የሚለው ሀረግ ለሚቀጥለው ሃሳብ አጽንዖት የሚሰጥ ነው:: አት: “በጥንቃቄ ስማ ግምታዊ እውቀት” ወይም “ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ”

የምሞትበትን ቀን አላውቅም

ይህ ይስሐቅ ቅርብ ጊዜ እንደሚሞት የሚያመለክት ነው:: አት: “ከማንኛውም ጊዜ ሊሞት ይሆናል”:: (ግምታዊ እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

ሞት

አካላዊ ሞትን ይገልጻል

Genesis 27:3

አጠቃላይ መረጃ

“ይስሐቅ ለታላቅ ልጁ ለዔሣው መመሪያልችን ይሰጣል”

የአደን መሣሪያህን

“የአደን መሣሪያዎችህን”

የፍላጻ ኩሮጆ

የፍላጻ ኩሮጆ የቀስቶች መሸከሚያ ነው:: አት: “የቀስቶች መሸከሚያ ኩሮጆ” (ግምታዊ እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

አድነህም አምጣልኝ

“የዱር እንስሳት አድነህ አምጣልኝ”

የምወደው ዓይነት ጣዕም ያለው ምግብ አዘጋጅተህ

“ጣዕም ያለው” የሚለው ቃል እጅግ በጣም ጣፋጭ የሆነውን ነገር ያመለክታል:: አት: “የምወደው ዓይነት የሥጋ ምግብ አዘጋጅልኝ” (ግምታዊ እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

እንዲመርቅህ

በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን አባት መደበኛ የሆነ መንገድ ልጆችን ይመርቃል

Genesis 27:5

“በወቅቱ”

በወቅቱ የሚለው ቃል ትኩረቱ ወደ ርብቃና ያዕቆብ መዞሩን ያሳያል:: (ግምታዊ እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

ርብቃም ይስሐቅ ለልጁ ለዔሣው ሲነግር ትሰማ ነበር

“ይስሐቅ ለልጁ የተናገረውን ርብቃ ትሰማ ነበር”

ዔሣው … ለማምጣት ሄደ:: ርብቃም ያዕቆብን እንዲህ አለችው

ዔሣው ከወጣ በኋላ ርብቃ የሰማችውን ለያዕቆብ ተናገረች:: አት: “ዔሣው ለማምጣት በወጣ ጊዜ ርብቃም ለያዕቆብ ተናገረች” (አያየዥ ቃላት ይመልከቱ)

ለዔሣው ለልጁ …. ለያዕቆብ ልጅዋን

ዔሣውና ያዕቆብ ሁለቱም የይስሐቅና የርብቃ ልጆች ናቸው አንድ ወላጅ አንዱን ልጅ ከሌላኛው ልጅ አብልጦ እንደሚወድ ተደርገው የእርሱ ልጅ እና የእርስዋ ልጅ ተብለው ተጠርተዋል::

ይሄው ተመልከት

“ይኼው ተመልከት” የሚለው ሀረግ ለሚቀጥለው ሃሳብ አጽንዖት የሚሰጥ ነው:: አት: “በጥሞና ስማ ግምታዊ እውቀት” ወይም “ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ”

እርሱም አለ ከመሞቴ በፊት በእግዚአብሔር ፊት እንዲመርቅህ ጥሩ ጣዕም ያለው ምግብ እንድበላ አዘጅልኝ

ይህ በጥቅስ ውስጥ የሚገኝ ጥቅስ ነው:: እንደተዘዋዋሪ ጥቅስ ሊገለጽ ይችላል አት: “ለዔሣውም ነገረው; ‘የዱር እንስሳ እንዲያድንና የሚወደውን ጣዕም የሥጋ ምግብ እንዲያዘጋጅለት’ ከዚያም ከመሞቱ በፊት በእግዚአብሔር ፊት የስሐቅ ዔሣውን እንዲባርከው” (በጥቅስ ውስጥ ጥቅሶችንና ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ ጥቅሶችን ይመልከቱ)::

አድነህም አምጣልኝ

“የዱር እንስሳት አድነህ ገድለህ አምጣልኝ”

የምወደው ዓይነት ጣዕም ያለው ምግብ አዘጋጅተህ

“የምወደው ዓይነት የሥጋ ምግብ አዘጋጅልኝ” ይህን በዘፍጥረት 27:4 እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ::

በእግዚአብሔር መገኘት እንዲመርቅህ

“በእግዚአብሔር ፊት እንዲመርቅህ”

Genesis 27:8

አጠቃላይ መረጃ

ርብቃ ለሁለተኛ ልጅዋ ለያዕቆብ መናገርዋን ቀጠለች

አሁንም

ይህ በዚያ ወቅት የሚለውን የሚናገር አይደለም ነገር ግን ለሚቀጥለው ዋና ነጥብ ትኩረት እንዲሰጥበት ነው::

እኔ በማዝዝህን ድምጼን ስማኝ

ርብቃ “ድምጼን” ያለችው የምትናገረውን ነገር ለማመልከት ነው:: አት: “ታዘዘኝ የምናገረውንም ነገር አድርግ” (ተዛማጅ ባሕሪይ የሚገልጽ ምትክ ቃል የመጠቀም ዘይቤ ይመልከቱ)

እነርሱንም አባትህ እንደሚወደው ዓይነት ጣፋጭ ምግብ አዘጋጅለታለሁ

ጣፋጭ የሚለው ቃል በጣም ጥሩ ጣዕም ያለውን ነገር ያመለክታል:: በዘፍጥረት 27:4 ተመሳሳይ ቃል እንዴት እንደተተረጐመ ይመልከቱ::

ወደ አባትህም ይዘህ ግባለት

“ከዚያም ወደ አባትህ ይዘህ ግባ”

እንዲበላ እንዲመርቅህ

ከበላ በኋላ ይመርቅሃል

ይመርቅህ ይሆናል

ምርቃት የሚለው ቃል አባት ልጆቹን የሚናገረው መደበኛ ምርቃት ነው

ከሞቱ በፊት

ከመመቱ በፊት

Genesis 27:11

እኔ ለስላሣ ነኝ

“የእኔ ገላ ለስላሣ ነው” ወይም “እኔ ጸጉራም አይደለሁም”

በምርቃት ፈንታ ርግማን አተርፋለሁ

መረገም ወይም መባረክ ምርቃት ወይም በረከት በአንድ ሰው ላይ እንደሚሆን ዕቃ ተደርገው ተነግረዋል አት ከዚያም ከዚህም የተነሣ ይረግመኛል ወይም አይባርከኝም (ዘይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)

Genesis 27:13

ልጄ ሆይ ማንኛውም ርግማን በእኔ ላይ ይድረስ

“ልጄ ሆይ መርገምህ በእኔ ላይ ይሁን” መረገም ርግማን በአንድ ሰው ጫንቃ ላይ እንደሚሆን ዕቃ ተደርጐ ተገለጾአል:: አት “ልጄ ሆይ አባትህ አንተን ከመርገም እኔን ይርገመኝ” (ዘይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)

ድምጼን ታዘዝ

ርብቃ “ድምጼን” ያለችው የምትናገረውን ነገር ለማመልከት ነው:: አት: “የሚናገርህን ታዘዝ” ወይም “ታዘዘኝ” (ተዛማጅ ባሕሪይ የሚገልጽ ምትክ ቃል የመጠቀም ዘይቤ ይመልከቱ)

እነርሱን አምጣልኝ

“ጠቦቶቹን አምጣልኝ”

ልክ አባቱ እንደሚወደው ዓይነት ጣፋጭ ምግብ አዘጋጀችለት::

ጣፋጭ የሚለው ቃል በጣም ጥሩ ጣዕም ያለውን ነገር ያመለክታል:: በዘፍጥረት 27:4 ተመሳሳይ ቃል እንዴት እንደተተረጐመ ይመልከቱ::

Genesis 27:15

ጠቦቶቹን ቆዳ በእጆቹ ላይ አለበሰችው

የጠቦቶች ቆዳዎች ጸጉር ነበረባቸው

የሠራችውን ጣፋጭ መብልና እንጀራውን ለልጅዋ ለያዕቆብ በእጁ ሰጠችው

“የሠራችውን ጣፋጭ መብልና እንጀራውን ለልጅዋ ለይዕቆብ ሰጠችው”

Genesis 27:18

እርሱም አለው

“እናም አባቱ መለሰው” ወይም “ይስሐቅም መለሰው”

አነሆኝ

“አዎን እየሰማሁ ነኝ” ወይም “አዎን ምንድነው?” በዘፍጥረት 22 1 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ

የተናገርከኝ ወይም ያዘዝከኝን አድርጌአለሁ

እንዳደርገው የነገርከኝን አድርጌአለሁ

አደን አድኜ ካመጣሁት ከፊሉ

“የታደነ” የምለው ቃል አንድ ሰው የዱር እንሰሳትን አድኖና ገድሎ የሚያቀርበውን ያመለክታል:: በዘፍጥረት 27:3 “የታደነ” የሚለው እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ::

Genesis 27:20

እርሱም አለው

ያዕቆብም መለሰው

አሳካልኝ

ይህ ፈሊጣዊ አነጋገር እግዚአብሔር ለሁኔታው ምክንያን እንደሆነ ይገልጻል:: አት: “በማድንበት ጊዜ እንዲሳካልኝ ረድቶኛል” (ፈሊጣዊ አነጋገሮች ይመልከቱ)::

በእርግጥ እውነተኛው ልጄ ዔሣው መሆንህን

“በእርግጥ ልጄ ዔሣው መሆንህን”

Genesis 27:22

ያዕቆብ ወደ አባቱ ወደ ይስሐቅ ቀረበ

“ያዕቆብ ወደ አባቱ ወደ ይስሐቅ ተጠጋ”

ይህ ድምጽ የያዕቆብ ድምጽ ነው

እዚህ ይስሐቅ የያዕቆብ ድምጽ ያዕቆብን እንደሚወክል ይናገራል፡፡ አት፡ “ድምጽህ የያዕቆብ ይመስላል” (ክፍልን እንደ ሙሉ ወይም ሙሉውን እንደ ክፍል የመግለጽ ዘይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)

እጆቹ ግን የዔሣው እጆች ናቸው

እዚህ ይስሐቅ የዔሣው እጆች ዔሣውን እንደሚወከሉ ይናገራል፡፡ አት፡ እጆች ግን የኤሣው እጆች እንደሆኑ ይሰሙኛል፡፡ (ክፍልን እንደ ሙሉ ወይም ሙሉውን እንደ ክፍል የመግለጽ ዘይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)

Genesis 27:24

እርሱም አለ

ይስሐቅ ልጁን ከመባረኩ በፊት ይህን ጥቃቄ ይጠይቀዋል:: አት፡ “ነገር ግን መጀመሪያ ይስሐቅ ጠየቀው” (የክስተቶች ቅደም ተከተል ይመልከቱ)

አድነህ ካቀረብክልኝ ልብላ

የታደነ የሚለው ቃል ሰዎች አድነውና ገድለው የሚያቀርቡትን የዱር እንሰሳ ያመለክታል:: በዘፍጥ 27:7 የታደነ እንዴት አንደተተረጐመ ይመልከቱ::

ጠጣም

“ይስሐቅ ጠጣ”

Genesis 27:26

እርሱም ልብሶቹን ካሸተተ በኋላ መረቀው

ልብሶች የኤሣው ልብሶች ሽታ እንዳሸቱ ግልጽ ነው:: አት: “እርሱም ልብሶቹን አሸተተ እናም ሽታው እንደ ዔሣው ልብሶች ሽታ ስለሆነ ባረከው” (ግምታዊ እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

አሸተተ

ይስሐቅ አሸተተ

ሽታ

ጠረን

ባረከው

“ከዚያም ባረከው” ይህ አባት ልጆቹን የሚባረከውን መደበኛ በረከት ያመለክታል::

እነሆ የልጄ ጠረን

“እነሆ” የሚለው ቃል ይህ እውነት ነው የሚለውን ለመግለጽ የተጠቀመ አበክሮአዊ ሥዕላዊ አገላለጽ ነው:: አት: “በእውነት የልጄ ጠረን”

እግዚአብሔር እንደባረከው

እዚህ በረከት የሚለው ቃል እግዚአብሔር በእርሻው መልካም ነገሮች እንዲሆኑና ፍሬያማ እንዲሆን እንዲያደርግ ነው:: አት: “ያም እግዚአብሔር ፍሬያማ እንዲያደርግ” (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)

Genesis 27:28

አጠቃላይ መረጃ

ይህ የይስሐቅ ባረኮት ነው ለኤሳው የተናገረው መሰለሙ ነገር ግን የተናገረው ለያዕቆብ ነው

ይስጥህ

እዚህ “ይስጥህ” ነጠላና ያዕቆብን የሚያመለክት ነው በረከቱ ግን ለያዕቆብ ትውልድም የሚሆን ነው:: (ሁለተኛ ሰው አጠቃቀምንና ክፍልን እንደ ሙሉ እና ሙሉን የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)

የሰማይን ጠል

ጠል በሌሊት በተክሎች ላይ የሚሆን የውሃ ጠብታ ነው:: በትርጉም ይህን ግልጽ ማድረግ ይቻላል:: አት: “ተክሎችዎን ለማጠጣት የሌሊት ጠል” (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

የምድርንም በረከት

ለም መሬት የመኖር መሬት ስብና ሀብታም እንደሆነች ተደርጐ ተገለጾአል:: አት: “እህልን የሚያመርት መልካም መሬት ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ”

የተትረፈረፈ እህልና አዲስ የወይን ጠጅ

“እህል”ና “ወይን” ያልተገለጹ እስከሆነ ድረስ ጠቅለል ባለ መልክ መግለጽ ይቻላል:: አት: “የተትረፈረፈ መብልና መጠጥ” (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

Genesis 27:29

አንተ…. ያንተ

እዚህ እነዚህ ተውላጤ ስሞች በነጠላ የተገለጹና የዕቆብን ያመለክታሉ በረከቱ ግን ለያዕቆብ ትውልድም ነው (ሁለተኛ ሰው አገላለጽንና ክፍልን እንደ ሙሉ እና ሙሉን እንደ ክፍል የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)

ሕዝቦች ተደፍተው እጅ ይንሡህ ወይም ይስገዱልህ

እዚህ ሕዝቦች ሰዎችን ያመለክታል አት የሁሉም ሕዝቦች ሰዎች ተደፍተው እጅ ይንሡህ:: (ተዛማጅ ተመሣሣይ ምትክ ቃላት የመጠቀም ዘይቤ ይመልከቱ)

ይስገዱልህ

ይህ ጐንበሥ በማለት አንድ ሰው አክብሮት መስጠትን ይገልጻል ምልክታዊ ድርጊት ይመልከቱ

የወንድሞችህ ጌታ ሁን

በወንድምችህ ላይ ጌታ ወይም ገዢ ሁን

ወንድሞችህ …የእናትህም ልጆች

ይስሐቅ ይህን በረከት በቀጥታ ለያዕቆብ ይናገራል ነገር ግን ይህ የያዕቆብ ትውልድ በኤሣው ትውልድና በሌሎች ማናቸውም የያዕቆብ ወንድሞች ትውልድ ላይ ገዢዎች እንደሚሆኑ ለእነርሱም ይሆናል፡፡ (ክፍል ለሙሉና ሙሉን ለክፍል የመጠቀም አገላለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)

የእናትህም ልጆች ይስገዱልህ

የእናትህም ልጆች የሰግዱልሃል

የምረግሙህ የተረገሙ ይሁኑ

ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል:: አት: “እግዚአብሔር የሚረግሙህን ሁሉ ይርገማቸው“ (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)

የሚባርኩህ የተባረኩ ይሁኑ

ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል:: አት: “እግዚአብሔር የሚባርኩህን ሁሉ ይባርካቸው“ (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)

Genesis 27:30

ያዕቆብም ገና ከአባቱ ዘንድ ሳይወጣ ወዲያውኑ

“ከአባቱን ከይስሐቅን ድንኳን እንደወጣ”

ጣፋጭ ምግብ

የምወደው ጣፋጭ ሥጋ በዘፍጥረት 27፡3 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ፡፡

ልጅህ ካደንሁት

እዚህ “ልጅህ” ኤሣው ካደነው ያዘጋጀውን ምግብ በትህትና ያቀረበበት መንገድ ነው:: (አንደኛ ሁለተኛና ሶስተኛ ሰው አገላለጽ ይመልከቱ)

ልጅህ ካደነው

የታደነ የሚለው ቃል ሰዎች አድነውና ገድለው የሚያቀርቡትን የዱር እንሰሳ ያመለክታል:: በዘፍጥ 27:7 የታደነ እንዴት አንደተተረጐመ ይመልከቱ::

ባርከኝ

ይህ አንድ አባት ልጆቹን የሚባርክበት መደበኛ መንገድ ያመለክታል

Genesis 27:32

ለእርሱም አለው

ዔሣውን አለው

ይስሐቅም ተንቀጠቀጠ

ይስሐቅም መንቀጥቀጥ ጀመረ

በአደን የታደነ

የታደነ የሚለው ቃል ሰዎች አድነውና ገድለው የሚያቀርቡትን የዱር እንሰሳ ያመለክታል:: በዘፍጥ 27:7 የታደነ እንዴት አንደተተረጐመ ይመልከቱ::

Genesis 27:34

ድምጹን ከፍ በማድረግ ምርር ብሎ አለቀሰ

የዔሣው ምሬት አንድ መራራ ጣዕም ካለው ነገር ጋር የሚመሳሰል ነበር:: አት: “በከፍተኛ ድምጽ አለቀሰ” (ዘይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)

ምርቃትህን ወስዶብሃል

ይህ ያዕቆብ የዔሣውን በረከት እንደወሰደ የሚገልጽ ምሳሌያዊ አገላለጽ ነው አት በአንተ ፈንታ እርሱን ባርከአለሁ (ዘይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)

Genesis 27:36

ያዕቆብ መባሉ የሚታወቅ አይደለምን?

ዔሣው በያዕቆብ ላይ ያለውን ቁጣ ለመጨመር ጥያቄ ይጠቀማል:: አት ያዕቆብ በእርግጥ ለወንድሜ ትክክለኛ ስም ነው:: (ቅኔያዊ ጥያቄዎችን ይመልከቱ)

ያዕቆብ

ተርጓሚዎች እንዲህ የሚለውን የግርጌ ማስታወሻ ይጠቀማሉ ያዕቆብ የሚለው ስም ተረከዙን ያዘ የሚል ትርጉም አለው በመሠረታዊው ቋንቋ ቃሉ አታላይ የሚል አንድምታ አለው::

ብኩርናዬን ወሰደብኝ

ይህ ብኩርና እንደ አንድ ዕቃ ከሰው እንደሚወሰድ አድርጐ ይናገራል:: አት: “የእኔ የሆነው ብኩርና በማታለሉ ምክንያት የእርሱ ሆኖአል” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)::

አሁን ደግሞ ምርቃቴን ቀማኝ

ይህ ምርቃት እንደ አንድ ዕቃ ከሰው እንደሚቀማ አድርጐ ይናገራል:: አት : “አታልሎህ በእኔ ፈንታ እርሱን እንዲትመርቅ አድረጐሃል” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)::

ለእኔ ያስቀረኼው ምንም ምርቃት የለም?

ያዕቆብን የባረከውን ዓይነት በረከት አባቱ እንደማይባርከው ዔሣው ያውቃል ይስሐቅ ያዕቆብን በሚባርክበት ጊዜ ሳይናገር የቀረው ካለ ዔሣው ይጠይቀዋል

ልጄ ለአንተ ምን ላደርግልህ እችላለሁ?

ይስሐቅ ጥያቄ በመጠቀም ምንም ሊያደርገው የሚችለው ነገር እንደሌለ በአጽንዖት ይናገራል:: አት “ለአንተ የማደርገው የቀረ ነገር የለም” (ቅኔ አዘል ጥያቄዎችን ይመልከቱ)

Genesis 27:38

አባቴ ሆይ በረከትህ አንዲት ብቻ ናትን?

ይህ በአዎንታዊ መንገድ ሊነገር ይችላል:: አባቴ ሆይ አንድ የቀረ መረከት ለእኔ የሚሆን አለህን?

Genesis 27:39

እርሱን አለው

ዔሣውን አለው

ቦታውን ተመልከት

ትኩረት አድርግ ስለቦታው የሚናገረው እውነትና ጠቃሚ ነው

ከምድር በረከት የራቀ

ይህ ስለምድር ለምነት የሚናገር ምሳለያዊ አነጋገር ነው አት ለም ያልሆነ መሬት

ለአንተ…. አንተ

በ27:39-4ዐ እነዚህ ተውላጤ ስሞች ነጠላና ዔሣውን ያመለክታሉ:: ነገር ግን ይስሐቅ የሚናገረው ለዔሣው ትውልድም የሚሆን ነው:: ክፍልን እንደ ሙሉና ሙሉን እንደ ክፍል የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ::

ከላይም ከሰማይ ጠል

ጠል በሌሊት በተክሎች ላይ የሚሆን የውሃ ጠብታ ነው:: በትርጉም ይህን ግልጽ ማድረግ ይቻላል:: አት: “ተክሎችዎን ለማጠጣት የሌሊት ጠል” (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

በሰይፍ ትኖራለህ

ሰይፍ ለአመጽ የሚቆም ነው:: አት: “ለመኖር የሚያስፈልግህን ለማግኘት ሰዎችን ትዘርፋለህ ትገድላለህ” (ተዛማጅ ተመሣሣይ ምትክ ቃል ስለመጠቀም ዘይቤ ይመልከቱ)

ቀንበሩ ከጫንቃህ ላይ ወዲያው ትጥላለህ

ይህ አንድ ጌታ እንዳለውና የጌታውም የበላይ አገዛዝ አንደሚሸከምበት ቀንበር እንደተጫነበት ተደርጐ ተነግሮአል አት ከግዛቱ ራስህን ነጻ ታወጣለህ:: (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)

Genesis 27:41

ዔሣውም በልቡ እንዲህ ብሎ አሰበ

“ልብ” ራሱ ዔሣውን ያመለክታል:: አት: “ዔሣው ለራሱ እንዲህ አለ” (ተዛማጅ ተመሣሣይ ምትክ ቃል የመጠቀም ዘይቤ ይመልከቱ) የአባቴ የለቅሶ ቀን ቀርቦአልና ይህ የቤተሰብ አባል ሲሞት አንድ ሰው የሚያዝንበት ቀናት ያመለክታል

የታላቅ ልጇ የኤሣው ሀሳብ ለርብቃ ተረገራት

ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል:: አት: “አንድ ሰው የዔሣውን ዕቅድ ለርብቃ ነገራት“ (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)

እይ

“ተመልከት” “አዳምጥ” “ለምናገረው ነገር ትኩረት ስጥ”

ራሱን እያረጋጋ ነው

ራሱን ጥሩ ስሜት እንዲሰማው እያደረገ ነው

Genesis 27:43

አሁንም

ይህ “አሁን ጊዜ” ማለት አይደለም:: ነገር ግን የሚቀጥለው አስፈላጊ ነጥብ ትኩረት እንዲሰጥበት ተጠቅሞአል::

ወደ ላባን ቶሎ ሽሽ

ቶሎ ከዚህ ሽሽ እናም ወደ ላባን ሂድ

ለጊዜ

ለተወሰነ ጊዜ

የወንድምህ ቁጣ እስኪበርድ

ወንድምህ እስኪበርድ

የወንድምህ ቁጣ ከአንተ እስኪመለስ

ያለ መቆጣት ቁጣ ከአንድ ሰው ወደ ሌላ አቅጣጫ እንደሚዞር ተደርጐ ተነግሮአል:: አት: “በአንተ ላይ መቆጣቱን እስኪተው ድረስ” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)

ሁለታችሁን በአንድ ቀን ለምን ሊጣ?

ርብቃ ሥጋትዋን ለመግለጽ ጥያቄ ትጠቀማለች አት ሁለታችሁን በአንድ ቀን ማጣት አልፈልግም! (ቅኔ አዘል ጥያቄዎችን ይመልከቱ)

ሁለታችሁን በአንድ ቀን አጣለሁ

ይህ የሚገልጸው ኤሣው ያዕቆብን ከገደለ እርሱ ደግሞ ገዳይ በመሆኑ ስለሚገድሉት ነው:: (ግምታዊ እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

አጣለሁ

ልጆቹዋ እንደሚሞቱባት የሚያመላክት ለዛ ያለ አገላለጽ ነው (ንኀብነት ወይም ለዛ ባለ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ አንድን ነገር የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)

Genesis 27:46

መኖር አስጠልቶኛል

ኤሣው የኬጢያውያን ሴት በማግባቱ ርብቃ መንኛ እንደተናደደች በማግነን ትኩረት መስጠትዋ ነው:: አት: “በማምረር ጠልቸዋለሁ” (hyperbole and Generalization/

የኬጢያውያን ሴት ልጆች

“እነዚህ የኬጢያውያን ሴቶች” ወይም “የኬጢያውያን ትውልጆች”

እንደነዚህ ሴቶች ከዚህ አገር ሴቶች ልጆች

“የአገሩ ሴቶች ልጆች” የአገሩ ሴቶች ማለት ነው:: አት: “በአገሩ የሚኖሩ እንደ እነዚህ ሴቶች” (ፈሊጣዊ አነጋገር ይጠቀሙ)

በሕይወት መኖር ለምኔ ነው?

ያዕቆብ ከኬጢያውያን ሴት ልጆች የሚያገባ ከሆነ ርብቃን ማነኛ እንደሚያስከፋት በማግነን ጥያቄ ትጠቀማለች:: አት: “ሕይወቴ የከፋ ይሆናል”